የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366 (1) ፣ 367 (1) እና 370 እንዲሁም በማይክሮ ፋይናንሱ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 (20.1) ፣ (20.4) እና (20.5) መሠረት የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
- ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
- 1.የማኅበሩ ስም፡- አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
- 2.የአክሲዮን ማኅበሩ አይነት፡- በማይክሮ ፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር
- 3.የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡-
ሀ) አማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ፣ ንግስት እሌኒ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር አዲስ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ፤
ለ) ስልክ ቁጥር፡- 0116376457/0116376668፣ ፖ.ሳ.ቁ፡- 211 ፣
ሐ) ድረ ገጽ፡- http://akufadamf.com
- 4.የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር፡- AM/BD/3/0004970/2014
- 5.የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- 372,849,000
- 6.የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- 263,210,000
- የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
- እ.አ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የተፈጸሙ የአክሲዮን ሽያጮችን እና ዝውውሮችን ተቀብሎ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመት የተቋሙን የውጭ ኦዲተር ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ ከ2025/2026 እስከ 2027/2028 ሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾም እና የስራ ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል እና አደላደል ላይ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተዘጋጅቶ የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
- እ.አ.አ የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የትርፍ ድርሻ እና እ.ኤ.አ የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት ስለሚከፈል ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ መወሰን፤
ማሳሰቢያ
- በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ ውክልና ወይም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን 3 (ሦስት) ቀናት በፊት በየትኛውም የማይክሮ ፋይናንሱ ቅርንጫፍ ወይም በማይክሮ ፋይናንሱ ዋና መስሪያ ቤት የሼር ሽያጭና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ ይዘው በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማይክሮ ፋይናንሱ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልታችሁ በመፈረም ተወካይ በመሾም በጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡
- በሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም በማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤትም ይሁን በቅርንጫፎቻችን ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የምትገኙ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116376457/0116376668 ይደውሉ፡፡
በተጨማሪም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ረቡዕ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እትም ገጽ 42 ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን!!
የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ
