አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እና ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ የደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 በአጋርነት የሚያዘጋጁት የሬድዮ ፕሮግራም ለማዘጋጀትና ለማሰራጨት የሥራ ውል ሥምምነት አደረጉ።
አኩፋዳ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ የፋይናንስ አገልግሎት ለማኅበረሰቡ የሚያቀርብ ሲሆን ከደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 ጋር በመተባበር የሬዲዮ ፕሮግራም በማሠራጨት በፋይናንስ አቅርቦት፣ ተደራሽነት፣ በንግድ ሥራና አስተዳደር እና በሥራ ፈጠራና የፋይናንስ ምንጭ ማፈላለግ ዙሪያ በስፋት ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ፕሮግራም እንዲሆን በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል።
የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት፣ አኩፋዳ ከ156 ሺህ በላይ ደንበኞች ያሉት አዳጊ የሕዝብ ተቋም በመሆኑ አገልግሎቱን በስፋት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ሚዲያን እንደ አንድ የቢዝነስ አጋር እንደሚጠቀም ገልጸዋል።
ደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 በበኩሉ የማህበረሰብን የኤኮኖሚ ዕድገት ከሚወስኑ የፋይናንስ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት በወጣቶች ሥራ ፈጠራና የፋይናንስ አቅርቦት፣ ህብረተሰብን በፋይናንስ-ነክ መረጃዎች ዐቅሙን በመገንባትና ግንዛቤ በመፍጠር የተጣለበትን ግዴታ መወጣት የሚያስችለው መሆኑን የደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ገበየሁ አሳውቀዋል።
ስኬትን በተግባር
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

