3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ
በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 366፣367፣370፣372፣392 እና 400 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 22 እና 23 መሰረት የአኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በደ/ብርሃን ከተማ በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
1. የማህበሩ መረጃዎች
የማህበሩ ስም | አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ |
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ | ደ/ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክ/ከተማ አጼዘርዓያቆብ ህንጻ 4ኛ ፎቅ |
የማህበሩ ዌብ ሳይት | https://www.Akufadamf.com |
የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር | AM/BD/3/0004970/2014 |
የአክሲዮን ማህበሩ አይነት | በማይክሮፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር |
የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ | 254,624,000.00 |
የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ | 131,780,000.00 |
2. የ3ኛ አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
- እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የተፈጸሙ የአክሲዮን ሽያጮችን እና ዝውውሮችን ተቀብሎ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2023/24 ሒሳብ አመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2023/24 ሒሳብ አመት የውጭ ኦዲተር ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾም እና የስራ ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል እና አደላደል ላይ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተዘጋጅቶ የቀረበውን መነሻ ሀሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2023/2024 ሒሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል አመታዊ የትርፍ ድርሻ እና እ.ኤ.አ 2024/2025 ሒሳብ ዓመት ስለሚከፈል አመታዊ የስራ ዋጋ ተወያይቶ መወሰን፤
- ለማህበሩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች ከማህበሩ የሚወስዷቸው ብድሮች እና ዋስትናዎች ተወያይቶ ስለማፅደቅ፤
- የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
- የ3ኛ አመታዊ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
- የማህበሩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል
- የጉባዔውን ቃለ ጉባኤ ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
ማሳሰቢያ፡-
- በጉባዔው በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች በደ/ብርሃን ከተማ እምዬ ምኒልክ ክፍለከተማ አጼዘርዓያቆብ ህንጻ 4ኛ ፎቅ የማይክሮፋይናንሱ አክሲዮን ሽያጭ እና አስተዳደር ክፍል ወይም በማይክሮፋይናንሱ ቅርንጫፎች በመገኘት በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ከጉባዔው ሶስት ቀን በፊት በአካል በመቅረብ የውክልና ቅጽ መሙላት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
- በውልና ማስረጃ ተረጋግጦ በጉባዔው ለመሳተፍ እና ድምጽ ለመስጠት ግልጽ ስልጣን የሚሰጥ የውክልና ማስረጃ የያዘ ተወካይ በእለቱ የውክልናውን ዋና እና ኮፒ እንዲሁም የባለአክሲዮኑን መታወቂያ ኮፒ ይዞ በመቅረብ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላል፡፡
- በማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት እና ቅርንጫፎች ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው የምትገኙ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ ዋናውን እና ኮፒ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ
የዳይሬክተሮች ቦርድ