አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለዋናው መስሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ከማርሚክ የማማከር ሥራዎች  ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል::

ስልጠናው በስትራቴጂክ አመራር፣በውጤታማ የቅርንጫፍ ሥራ አመራር፣በደንበኞች ግንኙነት፣በብድር  ስጋት ሥራ አመራር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያታኮረ ነው::

ስልጠናው በማርሚክ የማማከር ሥራዎች ድርጅት መስራች እና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ዶ/ር እመቤት መለሰ እና ሌሎች ተባባሪ አሰልጣኞች ይሰጣል::

ስልጠናው ከሐምሌ 12-13፣ 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ኢትዮ በርኖስ ሆቴል መሰጠቱን ይቀጥላል::

ስኬትን በተግባር!
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top