Asamere Arkese

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለዋናው መስሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ከማርሚክ የማማከር ሥራዎች  ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል:: ስልጠናው በስትራቴጂክ አመራር፣በውጤታማ የቅርንጫፍ ሥራ አመራር፣በደንበኞች ግንኙነት፣በብድር  ስጋት ሥራ አመራር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያታኮረ ነው:: ስልጠናው በማርሚክ የማማከር ሥራዎች ድርጅት መስራች እና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ዶ/ር እመቤት መለሰ እና ሌሎች ተባባሪ አሰልጣኞች ይሰጣል:: ስልጠናው ከሐምሌ 12-13፣ 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ኢትዮ በርኖስ ሆቴል መሰጠቱን ይቀጥላል:: ስኬትን በተግባር!አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለዋናው መስሪያ ቤት የሥራ ኃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ከማርሚክ የማማከር ሥራዎች  ድርጅት ጋር በመተባበር ስልጠና እየሰጠ ይገኛል:: ስልጠናው በስትራቴጂክ አመራር፣በውጤታማ የቅርንጫፍ ሥራ አመራር፣በደንበኞች ግንኙነት፣በብድር  ስጋት ሥራ አመራር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያታኮረ ነው:: ስልጠናው በማርሚክ የማማከር ሥራዎች ድርጅት መስራች እና ዋና ሥራ አሥፈፃሚ ዶ/ር እመቤት መለሰ እና ሌሎች ተባባሪ አሰልጣኞች ይሰጣል:: ስልጠናው ከሐምሌ 12-13፣ 2018 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ኢትዮ በርኖስ ሆቴል መሰጠቱን ይቀጥላል:: ስኬትን በተግባር!አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለሠራተኞች ስልጠና እየሰጠ ነው ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና ሰጠ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በዓመታዊው የዕቅድ አፍፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ በ2025/26 በጀት ዓመት በአጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እውቅና ሰጠ። የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ እና የተቋሙ ተ/ዋና ሥራ አስፍፃሚ አቶ ካሳው ሓይሉ ለተሸላሚዎቹ የዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና ሠርተፍኬት አበርክተዋል። ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ በ2025/26 በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን አስታውሰው፣ በቀጣይም መላው የተቋሙ ማኅበረሰብ  በሁሉም መመዘኛዎች ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። ሐምሌ 10 እና 11 በኢትዮ በርኖስ ሆቴል የተካሄደው ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የተቋሙ የቦርድ አባላት እና ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት እና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መመሪያዎችን በመስጠት ተጠናቋል። ስኬትን በተግባር!አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና ሰጠ Read More »

የተከበራችሁ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ባለአክሲዮኖች እና አክሲዮን ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ

የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መቋቋሙ እና በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ከሃምሳ (50) በላይ ባለአክሲዮን ባላቸው ማኅበራት (ኩባንያዎች) በባለ ሥልጣኑ መመዝገብ እንዳለባቸው የሚያስገድድ መመሪያ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የመመዝገብ ግዴታ ያለበት የአክሲዮን ማኅበር እስከ ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ. እስከ November 25/2025 ድረስ የመመዝገብ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ከኅዳር 17 ቀን 2018 ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ. እስከ November 26/2025 ጀምሮ ምንም ዓይነት የአክሲዮን ሽያጭ፡ ዝውውርና የውስጥ ግዥ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን እና ይህ ሳይሆን ቢቀር በወንጀል ጭምር የሚያስቀጣ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ኩባንያችን አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ሰዓት በምዝገባ ሂደት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምዝገባው ተጠናቆ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት እስከምንቀበል ወይም ባለሥልጣኑ የተለየ መመሪያ አውጥቶ ሽያጭ እስካልፈቀደ ድረስ ማናቸውም የአክሲዮን ግዥ እና ዝውውር የቆመ እና በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡                                                                              ስኬትን በተግባር!                                                                                            አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

የተከበራችሁ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ባለአክሲዮኖች እና አክሲዮን ለመግዛት ፍላጎት ያላችሁ በሙሉ Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ እ.ኤ.አ. በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ከ466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ቻለ!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በዛሬው ዕለት ኅዳር 14/2018ዓ.ም የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። የጉባኤው ታዳሚዎች በተገኙበት የ2024/25 ዓመታዊ ሪፖርትና ተያያዥ አጀንዳዎች ቀርበው የጸደቀ ሲሆን በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በቁልፍ የፋይናንስ መለኪያዎች ስኬታማ ውጤት ያስመዘገበ መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ ገልጸዋል፡፡ አቶ ተፈራ በሪፖርታቸው እንደገለጹት የማይክሮ ፋይናንሱ የተቀማጭ ገንዘብ በሒሳብ ዓመቱ ብር 2.3 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ እድገት አሳይቷል፤ የብድር ሥርጭት መጠኑ እ.ኤ.አ በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ ብር 2.8 ቢሊዮን ማቅረብ የታቻለ ሲሆን በሒሳብ ዓመቱ የተከናወነው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ75% ጭማሪ አሳይቷል።                                                                                     የማይክሮ ፋይናንሱ ጠቅላላ ገቢ ከብር 466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ እድገት አሳይቷል፡፡ ማይክሮ ፋይናንሱ አጠቃላይ ሀብቱን ከብር 2.7 ቢሊዮን በላይ ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ42% ዕድገት አሳይቷል። በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ካፒታል ከብር 321.7 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 83% የሚሆነው የተከፈለ የአክሲዮን ካፒታል ነው። ይህም ከባለፈው ሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ100% በላይ እድገት በማስመዝገብ ከፍተኛ እመርታን አሳይቷል። ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2024/25 ከታክስ በፊት ከብር 69.3 ሚሊዮን በላይ ማትረፍ የቻለ ሲሆን ካለፈው ሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ44% ጭማሪ አስመዝግቧል።                                                                                                                                              በአጠቃላይ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ፣ የፋይናንስ ተደራሽነት በማስፋት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ሰፊ የማሻሻያ መርሐ-ግብራትን በመተግበር በአነስተኛ ፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የገበያ ድርሻ በማድረግ ላይ ይገኛል። የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪው አካል ከሚያወጣቸው የሕግ ለውጦች ጋር እራሱን በፍጥነት እያላመደ እና ከለውጦቹ ጋር እየተራመደ እ.ኤ.አ በ2024/25 ሒሳብ ዓመትም በኦፕሬሽናል ሥራዎች፣ በፋይናንስ እና በተቋም ግንባታ መለኪያዎች ዕመርታዊ ለውጥ በማስመዘወገብ ዘላቂነት ያለው እድገት እያመጣ መሆኑን አሳይቶበታል፡፡                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                                           አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ                                                           ስኬትን በተግባር!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ እ.ኤ.አ. በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ከ466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ቻለ! Read More »

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ. ማ የባለአክሲዮኖች  4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ እያከናወነ ነው::

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ. ማ የባለአክሲዮኖች  4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ዛሬ ኅዳር 14 ቀን 2018   ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ  ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጉባኤውን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ. ማ የባለአክሲዮኖች  4ኛ ጠቅላላ ጉባኤ እያከናወነ ነው:: Read More »

እንኳን ደስ አላችሁ!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ በሁሉም ቅርንጫፎች የኮር-ባንኪንግ ትግበራ ከጀመረ ቆይቷል። አሁን ደግሞ ከዛሬ ከጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም ቅርንጫፍ የገንዘብ ዝውውር/ግብይት (Inter-Branch)ማድረግ የሚችሉ መሆኑን ስንገልጽ በታላቅ ደስታ ነው።   በመሆኑም ደንበኞች በ53ቱም ቅርንጫፎች እርስዎ ካሉበት ሆነው ወደ የትኛውም የአኩፋዳ ቅርንጫፍ ገንዘብ ማስገባት፣ ወጪ ማድረግናገንዘብ ማስተላለፍ የሚችሉ መሆኑን እናበስራለን።   አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማስኬትን በተግባር!

እንኳን ደስ አላችሁ! Read More »

ለተከበራችሁ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366 (1) ፣ 367 (1) እና 370 እንዲሁም በማይክሮ ፋይናንሱ መመስረቻ ጽሑፍ አንቀጽ 20 (20.1) ፣ (20.4) እና (20.5) መሠረት የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ኅዳር 14 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡                                                            1.ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች     1.1. የማኅበሩ ስም፡- አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ    1.2. የአክሲዮን ማኅበሩ አይነት፡- በማይክሮ ፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር                                          1.3. የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡- ሀ) አማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ እምዬ ምኒልክ ክፍለ ከተማ፣ ንግስት እሌኒ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር አዲስ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ፤ ለ) ስልክ ቁጥር፡- 0116376457/0116376668፣ ፖ.ሳ.ቁ፡- 211 ፣ ሐ) ድረ ገጽ፡- http://akufadamf.com    4.የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር፡- AM/BD/3/0004970/2014     1.5.የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡-   372,849,000  6. የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡-    263,210,000                                                          የባለአክሲዮኖች 4ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች                                                                                 2.1. እ.አ.አ እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የተፈጸሙ የአክሲዮን ሽያጮችን እና ዝውውሮችን ተቀብሎ ማፅደቅ፤                            2.2. እ.አ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤                           2.3. እ.አ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመት የተቋሙን የውጭ ኦዲተር ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤                              2.4. እ.አ.አ ከ2025/2026 እስከ 2027/2028 ሒሳብ ዓመት የውጭ ኦዲተር መሾም እና የስራ ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ ማፅደቅ፤         2.5. እ.አ.አ የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል እና አደላደል ላይ በዳይሬክተሮች ቦርድ ተዘጋጅቶ የቀረበውን                              የውሳኔ ሀሳብ ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤                                                                                                  2.6. እ.አ.አ የ2024/2025 ሒሳብ ዓመት ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ የትርፍ ድርሻ እና እ.ኤ.አ የ2025/2026                  ሒሳብ ዓመት ስለሚከፈል ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ መወሰን፤ ማሳሰቢያ                                                                                                                                                                 1.በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ ውክልና ወይም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ቀን 3 (ሦስት) ቀናት በፊት በየትኛውም የማይክሮ ፋይናንሱ ቅርንጫፍ ወይም በማይክሮ ፋይናንሱ ዋና መስሪያ ቤት የሼር ሽያጭና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ማንነታችሁን የሚያሳይ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ ይዘው በአካል በመቅረብ ለዚሁ ዓላማ በማይክሮ ፋይናንሱ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልታችሁ በመፈረም ተወካይ በመሾም በጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ ነው፡፡                                                                                                                                                                                                              2.በሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም በማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤትም ይሁን በቅርንጫፎቻችን ቀርባችሁ ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የምትገኙ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ ዋና እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116376457/0116376668 ይደውሉ፡፡ በተጨማሪም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ረቡዕ ጥቅምት 19 ቀን 2018 ዓ.ም እትም ገጽ 42 ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን!!   የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለተከበራችሁ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ Read More »

እንኳን ለ3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር አደረሳችሁ!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በዝቅተኛና በመካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የቁጠባ፣ የብድር እና የማይክሮ ኢንሹራንስ አገልግሎት ለማቅረብ በ1,886 ባለአክሲዮኖችና በብር 33,768,000 የተፈረመ መነሻ ካፒታል በመያዝ ዋና መሥሪያ ቤቱን ደብረብርሃን ከተማ በማድረግ ጥቅምት 12 ቀን 2015 ዓ.ም በይፋ ሥራውን የጀመረ ተቋም ነው። በአገራችንም ከመደበኛው የባንክ አገልግሎት በተጓዳኝ የአነስተኛ ገንዘብ ቁጠባና ብድር እየተስፋፋ ይገኛል። ይሁን እንጂ ከ130 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ባላት ኢትዮጵያ ከ55 ያልዘለሉ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ተደራሽ የመሆናቸው ዕድል እጅግ ውሱን እንደሆነ እንገነዘባለን። ይህን የሕዝቡን የመልማት ፍላጎት እና የፋይናንስ ተደራሽነት አለመጣጣም ለመቀነስ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ስትራቴጂያዊ የፋይናንስ አቅርቦት ላይ እየሠራ ይገኛል። ተቋማችን በ7 ክልሎች 53 ቅርንጫፎች በመክፈት 170,000 ደንበኞችን ማፍራት ችሏል። የተቋማችን ባለአክሲዮኖች ቁጥር 6,104 የደረሰ ሲሆን ተቋማችን ገልግሎቶቹን ለደንበኞቻችን ምቹ እንዲሆኑ ለማስቻል የኮር ባንኪንግ አገልግሎትን ሁሉም ቅርንጫፎች በሲስተም መስራት ጀምረዋል። ከተመሠረተ ጀምሮ ከ3.3 ቢሊዮን ብር በላይ ለደንበኞቹ ብድር ከ20,000 በላይ ለሚሆኑ ደንበኞቹ ብድር በመስጠት በተለይም ለግብርና ሥራ፣ ለልዩ ልዩ ኢንተርፕራይዞች የንግድ ሥራ ማንቀሳቀሻ፣ ለቋሚ ንብረት ማፍሪያ፣ ለቢዝነስ ሥራ ማስፋፊያ፣ ለሴት ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፣ ከአካል ጉዳት ጋር ለሚኖሩ የማኅበረሰባችን ክፍሎች የፋይናንስ አቅርቦት ላይ ትኩረት በማድረግ ለአገርና ወገን ዕድገት እየሰራን እንገኛለን። ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ከመጠቀም አንጻር የዲጂታል ባንኪንግ (የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን ቸምሮ ሌሎች በርካታ አማራጮችን የያዘ) መተግበሪያ አልምቶ ወደ ሥራ ለማስገባት ዝግጅቱን አጠናቋል። በቅርቡም በይፋ ለደንበኞቻችን መገልገያነት የምናውላቸው መሆኑን 3ኛ ዓመት የምሥረታ ዕለታችንን ስናከብር ማብሰራችን ኩራት ይሰማናል። በመሆኑም የአኩፋዳ 3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር ተጀምሯል። በዚህ መርሐ-ግብር ላይ ልዩ ልዩ መሰናዶዎችን በማከናወን የምናከብር ሲሆን፣ ዛሬ ጥቅምት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በደብረብርሃን ከተማ የከተማ ማስዋብና ጽዳት በማድረግ በይፋ አስጀምረናል። በቀጣይም በልዩ ልዩ ኹነቶች እያከበርንና ለማኅበረሰባችን የበጎ ፍቃድ አገልግሎት እንሰጣለን። አኩፋዳ ከ460 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞች የሥራ ዕድል የፈጠረ ሲሆን፣ በቀጣይም በዋና ዋና የዕድገት ዘርፎች ላይ የፋይናንስ አቅርቦትና ተደራሽነታችንን እያሳደግን አገር እንገነባለን። ለመላው የአኩፋዳ ባለአክሲዮኖች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ፣ በመላው ኢትዮጵያ የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን፣ የተዉኣማችን የሥራ መሪዎች፣ ታታሪ ሠራተኞቻችን እና መላው ደጋፊና አጋሮቻችን እንኳን ለ3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አደረሳችሁ፣ አደረሰን! አቶ አብርሃም ወዳጆየአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ስኬትን በተግባር!

እንኳን ለ3ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል አከባበር አደረሳችሁ! Read More »

Scroll to Top