የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ አድራሻ፡-በአማራ ብሔራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ የዋና ንግድ ምዝገባ ቁጥር AM/BD/3/0004970/2014፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሥራ ፈቃድ ቁጥር MF/055/2022፣ የተፈረመ ካፒተል ብር 33,768,000.00 (ሰላስ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ብር) ሲሆን የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡ 00 ሠዓት ጀምሮ በአማራ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አዳራሽ ውስጥ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይንም በወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡

የሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች

  • የጉባኤውን አጀንዳዎች ማፅደቅ
  • በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ የአክሲዮን ዝውውርን ማፅደቅ
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ የ 2022/2023 ዓመታዊ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
  • የውጪ ኦዲተሮች የ 2022/2023 ዓመታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማድመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዓመታዊ የሥራ ዋጋና አበልን መወሰን
  • የዳይሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ማካሄድ
  • የጉባኤውን ቃለጉባኤ ማጽደቅ

ሁለተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች

  • የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፤
  • የተቋሙን የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል፤
  • በዓይነት የተደረገው መዋጮ ግምትን እና በግምቱ ላይ የተከናወነ የኦዲት ሪፖርትን ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
  • የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፤

ማሳሰቢያ፦

1. በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡ 2. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ ደብረ ብርሃን ከተማ ፃድቃኔ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ የውክልና ቅፅ በመሙላት ወይም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ በስብሰባ ላይ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ወይም የሞግዚትነት ማስረጃ በማቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top