አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ እ.ኤ.አ. በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ከ466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ቻለ!
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ በዛሬው ዕለት ኅዳር 14/2018ዓ.ም የባለአክሲዮኖች 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሄደ። የጉባኤው ታዳሚዎች በተገኙበት የ2024/25 ዓመታዊ ሪፖርትና ተያያዥ አጀንዳዎች ቀርበው የጸደቀ ሲሆን በተጠናቀቀው የሒሳብ ዓመት በቁልፍ የፋይናንስ መለኪያዎች ስኬታማ ውጤት ያስመዘገበ መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ ገልጸዋል፡፡ አቶ ተፈራ በሪፖርታቸው እንደገለጹት የማይክሮ ፋይናንሱ የተቀማጭ ገንዘብ በሒሳብ ዓመቱ ብር 2.3 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ይህም ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ40 በመቶ እድገት አሳይቷል፤ የብድር ሥርጭት መጠኑ እ.ኤ.አ በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ማጠናቀቂያ ድረስ ብር 2.8 ቢሊዮን ማቅረብ የታቻለ ሲሆን በሒሳብ ዓመቱ የተከናወነው ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነጻጸር በ75% ጭማሪ አሳይቷል። የማይክሮ ፋይናንሱ ጠቅላላ ገቢ ከብር 466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን ከባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በእጥፍ እድገት አሳይቷል፡፡ ማይክሮ ፋይናንሱ አጠቃላይ ሀብቱን ከብር 2.7 ቢሊዮን በላይ ያስመዘገበ ሲሆን ይህም ከባለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ42% ዕድገት አሳይቷል። በሒሳብ ዓመቱ መጨረሻ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ካፒታል ከብር 321.7 ሚሊዮን በላይ የደረሰ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 83% የሚሆነው የተከፈለ የአክሲዮን ካፒታል ነው። ይህም ከባለፈው ሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ100% በላይ እድገት በማስመዝገብ ከፍተኛ እመርታን አሳይቷል። ተቋሙ እ.ኤ.አ በ2024/25 ከታክስ በፊት ከብር 69.3 ሚሊዮን በላይ ማትረፍ የቻለ ሲሆን ካለፈው ሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ44% ጭማሪ አስመዝግቧል። በአጠቃላይ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማዊ አቅሙን በማሳደግ፣ የፋይናንስ ተደራሽነት በማስፋት እና ማኅበራዊ አገልግሎት ላይ ሰፊ የማሻሻያ መርሐ-ግብራትን በመተግበር በአነስተኛ ፋይናንስ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያለውን የገበያ ድርሻ በማድረግ ላይ ይገኛል። የፋይናንስ ተቋማት ተቆጣጣሪው አካል ከሚያወጣቸው የሕግ ለውጦች ጋር እራሱን በፍጥነት እያላመደ እና ከለውጦቹ ጋር እየተራመደ እ.ኤ.አ በ2024/25 ሒሳብ ዓመትም በኦፕሬሽናል ሥራዎች፣ በፋይናንስ እና በተቋም ግንባታ መለኪያዎች ዕመርታዊ ለውጥ በማስመዘወገብ ዘላቂነት ያለው እድገት እያመጣ መሆኑን አሳይቶበታል፡፡ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ስኬትን በተግባር!
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ እ.ኤ.አ. በ2024/25 ሒሳብ ዓመት ከ466.4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰብ ቻለ! Read More »









