Es D

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶኒያ የ400000.00(አራት መቶ) ሺ ብር ድጋፍ አደረገ በሁለት አመት ውስጥ ከአርባ ሶስት በላይ ቅርጫፍ ማድረስ የቻለውና ካፒታሉንም ሆነ የባለአክሲዮን ቁጥሩን በከፍተኛ ፍጠነት እያሳደገ ያለው አኩፋዳ ገና በመጀመሪያ ዓመቱ የትርፍ ክፍፍል ማድረግ የቻለ ብቸኛው ተቋም ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ሁሉም ማኅበረሰብ ባለአክሲዮን እንዲሆን ህልም ይዞ የተነሳው አኩፋዳ ከ10000.00 (አሥር ሺ) ብር ጀምሮ ባለአክሲዮን መሆን እንደሚቻል በመንገር ጥሪውን ያስተላልፋል ። አገልግሎቱን በኮር ባንኪንግ በማገናኘት ቀልጣፍ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በሳል በሆኑ ቦርዶችና ዳይሬክተሮች የሚመራው አኩፋዳ በቅርቡ ዋና መስሪያ ቤቱን ለመገንባት ቦታ በመረከብ የግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል… አኩፋዳ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ ተቋም ሲሆን ሀገራዊ የሀብት ማሰባሰብ አካል ለመሆን በማሰብ  ለመቄዶኒያ  የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን  መርጃ ማዕከል የ400000.00 (አራት መቶ ሺ) ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ስኬትን በተግባር !!!!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ። Read More »

Job Title: Director, Information Technology Directorate

Job Grade: 15 Purpose of the Job: To ensure the Akufada’s leadership in delivering technology-supported, efficient and convenient products and services by leading the development and management of the Akufada’s information system and technology resources. The position is also responsible for ensuring rational and data-driven decision-making at all levels of the institution by leading the development and implementation of a user-friendly and flexible decision-support system. Results and Outputs Unit’s Outcome Areas that relate to this job Key expected result / outputs / Report/output provided Frequency of output Secured IT environment Put in place IT security objectives, policies and procedures and effective enforcement of the same Annual budget and work plan for the function  Annually Effective and efficient IT Service delivery Set up standards and effectively implement them Security risk assessment report Semi-Annually Integrated and holistic IT solutions Design and implement IT projects aligned with Akufada’s objective Project status report As needed   Preferred service quality Set up SLA (Service Level Agreement) Work performance report (addresses the whole functional unit Quarterly   IT solution innovation Enabling the MFI through innovative IT application recommendations and proposals Staff performance evaluation report Semi-annually Duties and Responsibilities Qualifications and experience Competencies Apply Via Email Address          hr@akufadamf.com Registration Only 7 days From  06/1/2025 To 12/1/2025

Job Title: Director, Information Technology Directorate Read More »

1. Job Title:    Director, Internal Auditor Directorates

Job Grade: 14 Purpose of the Job: To ensure that the overall operation and IT environment is in line with the Akufada’s policies and procedures and applicable laws and regulations. The position is also responsible for ensuring the adequacy, strength and uniformity of the internal control system of the MFI and for providing an independent, objective assurance and consulting service to the Executive Management and the Board of Directors with the view to strengthening the MFI’s internal control and governance environment. Results and Outputs: Unit’s Outcome Areas that relate to this job Key expected result / outputs / Report/output provided Frequency of output Effective internal control system to enhance risk management and governance Comprehensive and relevant risk-based Audit, Inspection and IT Audit (Internal Audit) programs Audit, Inspection and IT Audit As required Objective assurance on adherence to relevant policies, procedure and regulatory directives and laws Timely and effective risk-based audit, inspection and Information Technology Audit Audit, Inspection and Information Technology Audit reports/findings   As per the annual Audit and Inspection Program/Plan Special investigation on frauds and embezzlements Special Investigation report   As required   Duties and Responsibilities Competencies: Qualifications and Experience: Email Address          hr@akufadamf.com    Registration Only 7 days From  06/1/2025 To 12/1/2025

1. Job Title:    Director, Internal Auditor Directorates Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ።

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን እሁድ ሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ በዕለቱም የማይክሮ ፋይናንሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ካሳሁን ደገፉ የተቋሙን የ2023/24 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ በጉባዔው እንደገለጹት በዚህ ፈታኝ ወቅት ተቋሙ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ የሚባል ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉንና የሒሳብ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሒሳብ ዓመቱ 48 ሚሊዮን ብር ከግብር በፊት ማትረፉን ለባለአክሲዮኑ አቅርበዋል፡፡ ጉባዔውም ከተገኘው ትርፍ ላይ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጭዎች ተቀንሰው ለማኅበራዊ አገልግሎት 4% በመመደብ ቀሪውን ትርፍ ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን በሚደርሰው ትርፍ ድልድል መሠረት አክሲዮኑን እንዲያሳድግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ካሳሁን ደገፉ በሰጡት ማሳሰቢያ ሁሉም ባለአክሲዮን ተቋሙን እንዲያጠናክር፣ እንዲደግፍና ያለውን የአክሲዮን ድርሻ እንዲያሳድግ በመጠየቅ ስኬትን በተግባር እንድንኖረው የተቋሙ ባለድርሻዎች ላደረጉት ድጋፍና አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ። Read More »

ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 366፣367፣370፣372፣392 እና 400 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 22 እና 23 መሰረት የአኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በደ/ብርሃን ከተማ በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 1. የማህበሩ መረጃዎች የማህበሩ ስም አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ደ/ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክ/ከተማ አጼዘርዓያቆብ ህንጻ  4ኛ ፎቅ የማህበሩ ዌብ ሳይት https://www.Akufadamf.com የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር AM/BD/3/0004970/2014 የአክሲዮን ማህበሩ አይነት              በማይክሮፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ 254,624,000.00 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ 131,780,000.00 2. የ3ኛ አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች ማሳሰቢያ፡-   አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ!

“እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ባሳለፍነው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ለዚህ ውጤት መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከታችሁ የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።በሂሳብ ዓመቱ ብር 232 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን በዓመቱ ውስጥ የነበረው የወጪ አፈፃመማችን 183 ሚሊዮን ብር ሲሆን 47 ሚሊዮን ብር ትረፍ አትር÷ል፡፡ ለተገኘው ትርፍ ተቋማችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂዎች ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።ተቋማችን በስምንት ክልሎች 42 ቅርንጫፍ በመክፈት ከ95,000 በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለ8250 ደንበኞች አቅርቧል፤ የተሰጡ ብድሮች ለግል ፍጆታ ብድር፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለግብርና ብድር፣ ለቤት መስሪያና ማደሻ እና ለተሽከርካሪ ግዥ ብድር ለማኅበረሰባችን ተደራሽ አድጓል፡፡ተቋማችን በ21 ሚሊዮን ብር ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተከፈለ ካፒታል ብር 136 ሚሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ የተቋሙ ሃብት ብር 1.9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡የተቋማችን የሦስት ዓመት መሪ ዕቅድን መሰረት አድርጎ እየተተገበረ የሚገኘው የሪፎርም ስራ ፍሬያማ በመሆኑ የተበላሹ ብድሮች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ተቋማችን ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን፤ እንዲሁም የወጪ ቅነሳ እንቅስቃሴያችን ውጤታማ እንዲሆን አስችሏል። ተቋማችን አገልግሎቶቹን ለደንበኞቻችን ምቹ እንዲሆኑ ለማስቻል የኮር ባንኪንግ እና አዳዲስ የድጅታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በመዘርጋት እውን ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም ለደንበኞቻችን አገልግሎትና ተያያዥ ሥራዎች መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ወጪን ለመቀነስ ያስችላል።በሌላ በኩል ባጠናቀቅነው ሂሳብ ዓመት የተቋማችን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች የገጠሙት ቢሆንም፣ እነዚህን ተግዳሮቶች በመቋቋም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻላችን የተቋማችንን ጥንካሬ ብሎም አይበገሬነት ማሳያ ነው።በተገኘው አመርቂ ውጤት በመበረታታት በአዲሱ ሒሳብ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በበለጠ ተነሳሽነትና ትጋት መስራት ይጠበቅብናል።የተቋማችን የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ሥራ አመራር አባላት የሚሰጡትን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና የላቀ አገልግሎት በማቅረብ የደንበኞቻችንን እርካታ ከፍ ለማድረግ በትጋት እየሠራን ሲሆን በመጨረሻም ደንበኞቻችን አብራችሁን በመሆን ለውጤቱ መሳካት ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ በድጋሚ እያመሰገንን፣ በ2017 ሂሳብ ዓመትም ተቋማችን ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በሁሉም ክልሎች በመክፈት 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ አክሲዮኖችን መሸጥ፣ 200,052 ደንበኞችን በማፍራት 3.3 ቢሊዮን ብር የተቀማጭን ገንዘብ በመሰብሰብ ለ20,002 የብድር ደንበኞች 3.6 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞች ያቀርባል። እንዲሁም የአክሲዮን ትርፉን በአንድ ሺህ ብር አምስት መቶ ብር ለማከፋፈል በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስስኬትን በተግባር!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ! Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቅያሪ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በደብር ብርሃን ጻድቃኔ ህንፃ 6ተኛ ወለል ላይ የነበረውን የዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ወደ አፃ ዘርዐ ያዕቆብ ህንፃ 4ተኛ ወለል ላይ ቀይሯል ፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቅያሪ አደረገ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ የዋና መሥሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የአርባ ሁለቱም ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸምና 2017 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት ዕቅድ ሐምሌ 27 እና 28 /2016 ዓ.ም ለሁለት (2) ተከታታይ ቀናት በኢትዮ በርኖስ ሆቴል ገመገመ፡፡ተቋሙ በችግር ዉስጥ ሆኖ እጅግ ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡን በማየት በቀጣይ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን በመክፈት የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ አቅጣጫ ተስጥቷል፡፡ለስኬታችን ክቡራን ባለአክሲዮኖቻችን ፡ደንበኞቻችን የግልና የመንግስት ድርጅቶች ፡የዳይሬክትር ቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ባለድሻ አካላት አበርክቷቸው ከፍ ያለ በመሆኑ በእግዚአብሔር አምላካችን ስም ስናመሰግናችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አደረገ። Read More »

የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ አድራሻ፡-በአማራ ብሔራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ የዋና ንግድ ምዝገባ ቁጥር AM/BD/3/0004970/2014፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሥራ ፈቃድ ቁጥር MF/055/2022፣ የተፈረመ ካፒተል ብር 33,768,000.00 (ሰላስ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ብር) ሲሆን የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡ 00 ሠዓት ጀምሮ በአማራ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አዳራሽ ውስጥ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይንም በወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ የሁለተኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች የሁለተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች ማሳሰቢያ፦ 1. በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡ 2. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ህዳር 29 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ ደብረ ብርሃን ከተማ ፃድቃኔ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ የውክልና ቅፅ በመሙላት ወይም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ በስብሰባ ላይ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ወይም የሞግዚትነት ማስረጃ በማቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ Read More »

የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ አድራሻ፡-በአማራ ብሔራ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ሸዋ ዞን፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ ቀበሌ 02፣ የዋና ንግድ ምዝገባ ቁጥር AM/BD/3/0004970/2014፣ የማይክሮ ፋይናንስ ተቋም ሥራ ፈቃድ ቁጥር MF/055/2022፣ የተፈረመ ካፒተል ብር 33,768,000.00 (ሰላስ ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ስልሳ ስምንት ሺ ብር) ሲሆን የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ታህሳስ 29 ቀን 2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡ 00 ሠዓት ጀምሮ በአማራ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ አዳራሽ ውስጥ ስለሚካሄድ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይንም በወኪሎቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ጊዜና ቦታ በስብሰባው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡የአንደኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳዎች የጉባኤውን አጀንዳ ማፅደቅ፤ የተቋሙን የመመስረቻ ፅሁፍ ማሻሻል፤ በዓይነት የተደረገው መዋጮ ግምትን እና በግምቱ ላይ የተከናወነ የኦዲት ሪፖርትን ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤ የጉባኤውን ቃለ ጉባኤ ማፅደቅ፤ ማሳሰቢያ፦ 1. በጉባኤው ላይ በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖችም ሆኑ ወኪሎች የታደሰ መታወቂያ፣ ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ይዛችሁ እንድትቀርቡ እናሳስባለን፡፡ 2. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ አስከ ታህሳስ 21 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ብቻ ደብረ ብርሃን ከተማ ፃድቃኔ ሕንፃ 6ኛ ፎቅ ከሚገኘው የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በመቅረብ የውክልና ቅፅ በመሙላት ወይም አግባብ ባለው የመንግስት አካል የተረጋገጠ በስብሰባ ላይ ለመሳተፍና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ወይም የሞግዚትነት ማስረጃ በማቅረብ በጉባኤው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማህበር የዳይሬክተሮች ቦርድ

የባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ጥሪ ማስታወቂያ Read More »

Scroll to Top