አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶኒያ የ400000.00(አራት መቶ) ሺ ብር ድጋፍ አደረገ
በሁለት አመት ውስጥ ከአርባ ሶስት በላይ ቅርጫፍ ማድረስ የቻለውና ካፒታሉንም ሆነ የባለአክሲዮን ቁጥሩን በከፍተኛ ፍጠነት እያሳደገ ያለው አኩፋዳ ገና በመጀመሪያ ዓመቱ የትርፍ ክፍፍል ማድረግ የቻለ ብቸኛው ተቋም ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ።
ሁሉም ማኅበረሰብ ባለአክሲዮን እንዲሆን ህልም ይዞ የተነሳው አኩፋዳ ከ10000.00 (አሥር ሺ) ብር ጀምሮ ባለአክሲዮን መሆን እንደሚቻል በመንገር ጥሪውን ያስተላልፋል ።
አገልግሎቱን በኮር ባንኪንግ በማገናኘት ቀልጣፍ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
በሳል በሆኑ ቦርዶችና ዳይሬክተሮች የሚመራው አኩፋዳ በቅርቡ ዋና መስሪያ ቤቱን ለመገንባት ቦታ በመረከብ የግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል… አኩፋዳ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ ተቋም ሲሆን ሀገራዊ የሀብት ማሰባሰብ አካል ለመሆን በማሰብ ለመቄዶኒያ የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የ400000.00 (አራት መቶ ሺ) ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ
ስኬትን በተግባር !!!!

