አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እ.አ.አ የ2024/25 ሒሳብ ዓመትን በስኬት ማጠናቀቁን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው።
ለዚህ ተግባራዊ ስኬት ውድ ባለአክሲዮኖቻችን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ፣ በሥራ አመራር ቦርድ አባላት ላቅ ያለ የቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ አመራር ለሰጣችሁ የስራ አመራር ቦርድ አባላት እንዲሁም ለውጤት የምትተጉ ቅርንጫፎቻችን፣ የተቋማችን የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ከምንም በላይ ግን የሒሳብ ዓመቱ ስኬት ዋነኛ ባለቤቶች የሥራ ፈጠራና የለውጥ የቢዝነስ ሥራ አንቀሳቃሽ፣ አርሶ አደር እና ወጣት ሴቶች ደንበኞቻችን ናቸው።
በያዝነው የሒሳብ ዓመት የተቋማችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና መላው ሠራተኞች ጠንካራ ጎኖቻችንን በማጎልበት እና የነበሩንን ውሱንነቶች በማሻሻል፣ መልካም አጋጣሚዎችን በንቃት በመጠቀም፣ እንዲሁም ከፊታችን የሚደቀኑ ፈተናዎችን በማሸነፍ፣ አሰራራችንን በኮርባንኪንግ እና በዲጂታል ባንኪንግ በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለራዕያችን መሳካት በትጋት እንደምንሰራ ቃል እየገባን፣ የተለመደው የደንበኞቻችን እና የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር እንዳይለየን በማክበር እጠይቃለሁ።
ለተገኘው ስኬት ዋነኛ ተዋናይ ለሆናችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን፣ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ለባለአክሲዮኖች እና ለውድ ሠራተኞቻችን ያለኝን ላቅ ያለ ምስጋናዬ እያቀረብኩ፣ አዲሱ የሂሳብ ዓመት ቀጣይነት ያለው ዕድገት የምናሳይበት እንዲሆን እመኛለሁኝ።
ስኬትን በተግባር!
አብርሃም ወዳጆ
ዋና ሥራ አስፈፃሚ

