እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!

ክቡራን የአኩፋዳ ደንበኞች፣ ባለአክሲዮኖች፣ ትጉኃን ሠራተኞቻችን እና መላው ኢትዮጵያውያን እና በመላው ዓለም የምትገኙ አጋሮቻችን እንኳን ለ2018 ዓ.ም በፍቅርና በመተሳሰብ አደረሳችሁ።

ይህን አዲስ ዘመን ስንቀበል ተቋማችን በአጭር ጊዜ በከፍተኛ የዕድገትና የውጤታማነት ምዕራፍ ላይ መሆኑ እጅግ አበረታች ነው።

በስትራቴጂ ያስቀመጥናቸውን መላውን የአገራችንን ማኅበረሰብ በተለይም የፋይናንስ ተደራሽነት ጉድለት ያለባቸውን አርሶ አደሮች፣ የገጠር ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፣ የከተማ ወጣቶች እና አነስተኛ ኢንቨስትመንቶችን በበቂ ሁኔታ ፋይናንስ ለማድረግ እየሠራን እንገኛለን።

ለዚህ ትልቅ የዕድገት ርዕይ ደንበኞቻችን እና አጋሮቻችን ከጎናችን እንደሚሆኑ በመተማመን አዲሱን ዘመን ጀምረናል።

ዘመኑ የፍሬ እና የውጤት እንዲሆን እየተመኘሁ መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቴን እገልፃለሁ።

መልካም በዓል🌼🌼🌼

አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ ገድሌ
የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top