በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተዘጋጀው ‘ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ’ በመላ አገሪቱ የፋይናንስ አቅርቦትን ለማጎልበት እና አነስተኛ አርሶ አደሮችን ብድር እንዲያገኙ ለመደገፍ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለግብርናው ዘርፍ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አቅርቦት በአጭር ጊዜ ማቅረቡን ገልፀው ለአርሶ አደራችን ለውጥና እድገት ብሎም ለአጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ተቋማችን የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ጨምረው ገልፀዋል።

