Asamere Arkese

የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እና ፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን አ.ማ የደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 በአጋርነት የሚያዘጋጁት የሬድዮ ፕሮግራም ለማዘጋጀትና ለማሰራጨት የሥራ ውል ሥምምነት አደረጉ። አኩፋዳ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ የፋይናንስ አገልግሎት ለማኅበረሰቡ የሚያቀርብ ሲሆን ከደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 ጋር በመተባበር የሬዲዮ ፕሮግራም በማሠራጨት በፋይናንስ አቅርቦት፣ ተደራሽነት፣ በንግድ ሥራና አስተዳደር እና በሥራ ፈጠራና የፋይናንስ ምንጭ ማፈላለግ ዙሪያ በስፋት ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ፕሮግራም እንዲሆን በጋራ ለመሥራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል። የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ወቅት፣ አኩፋዳ ከ156 ሺህ በላይ ደንበኞች ያሉት አዳጊ የሕዝብ ተቋም በመሆኑ አገልግሎቱን በስፋት ለሕዝብ ተደራሽ ለማድረግ ሚዲያን እንደ አንድ የቢዝነስ አጋር እንደሚጠቀም ገልጸዋል። ደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 በበኩሉ የማህበረሰብን የኤኮኖሚ ዕድገት ከሚወስኑ የፋይናንስ ተቋማት ጋር አብሮ በመስራት በወጣቶች ሥራ ፈጠራና የፋይናንስ አቅርቦት፣ ህብረተሰብን በፋይናንስ-ነክ መረጃዎች ዐቅሙን በመገንባትና ግንዛቤ በመፍጠር የተጣለበትን ግዴታ መወጣት የሚያስችለው መሆኑን የደብረብርሃን ፋና ኤፍ.ኤም 94.0 ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም ገበየሁ አሳውቀዋል። ስኬትን በተግባርአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ Read More »

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተዘጋጀው የፋይናንስ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ።

በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተዘጋጀው ‘ብሔራዊ የግብርና ፋይናንስ ትግበራ ፍኖተ ካርታ’ በመላ አገሪቱ የፋይናንስ አቅርቦትን ለማጎልበት እና አነስተኛ አርሶ አደሮችን ብድር እንዲያገኙ ለመደገፍ ቁልፍ መሣሪያ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው  አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለግብርናው ዘርፍ ከ120 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አቅርቦት በአጭር ጊዜ ማቅረቡን ገልፀው ለአርሶ አደራችን ለውጥና እድገት ብሎም  ለአጠቃላይ  ኢኮኖሚያዊ  ዕድገት  ተቋማችን  የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያደርግ ጨምረው ገልፀዋል።                               

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ በግብርና ሚኒስቴር እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በተዘጋጀው የፋይናንስ የማስጀመሪያ ፕሮግራም ላይ ተሳተፉ። Read More »

“የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫችን ነው”

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ከተቋሙ የሥራ አመራር አባላት እና ከቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች ጋር የ2024/25 ሒሳብ ዓመት የአፈጻጸምን አስመልክቶ የምክክር መድረክ አካሄደ። በመድረኩ የተገኙት አቶ ተፈራ ወንድማገኘሁ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ካሣሁን ደገፉ ከ45ቱ ቅርንጫፎች ጋር በጋራ የዓመቱን አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ በተያዘው የ2025/26 ተቋማዊ ውጤታማነትን እና ትርፋማነትን በማረጋገጥ ለባለአክሲዮኖች እና ማኅበረሰብ እድገት መሥራት ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን አቅጣጫ ሰጥተዋል። የቦርዱ ሰብሳቢ አክለውም አኩፋዳ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ በ7 ክልሎች ከ150 ሺህ በላይ ደንበኞቹን ማገልገል መጀመሩ ትልቅ ስኬት ሲሆን፣ በሂደት ተደራሽነቱን፣ የደንበኞች አያያዝ ሥርዓቱን እና ቅልጥፍናውን በማላቅ ተመራጭ የፋይናንስ ተቋም ለመሆን የጀመረው ጉዞ አመርቂ ነው ብለዋል። ተቋሙ የፋይናንስ አሰራሩን ይበልጥ ቀልጣፋ ለማድረግ ቴክኖሎጅን ከጅምሩ ለመተግበር አስደሳች ስራዎችን ሲሰራ ቆይቷል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ አብርሃም ወዳጆ፣ “የአገልግሎት ቅልጥፍናችን እንዲሻሻልና የደንበኞቻችንን እርካታ ለማሳደግ የቴክኖሎጅ (ኮር ባንኪንግ፣ የሞባይል ባንኪንግ፣ ወዘተ) በተሟላ ደረጃ ለመተግበር የሚያስችሉ ሥራዎች መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል። ማይክሮ ፋይናንስ ተቋሙ 45 ቅርንጫፎችን በመክፈት የፋይናንስ አቅርቦት እያደረገ ይገኛል ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፣ በአጭር ጊዜ 450 ሠራተኞችን በመቅጠር ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ብለዋል። በማጠቃለያውም በተጠናቀቀው ሒሳብ ዓመት የተሻለ የኦፕሬሽን አፈጻጸም ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች ዕውቅና እና ምስጋና ተበርክቶላቸዋል

“የፋይናንስ አገልግሎት ተደራሽነት ቁልፍ የትኩረት አቅጣጫችን ነው” Read More »

እንኳን ደስ አላችሁ!እንኳን ደስ አለን!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እ.አ.አ  የ2024/25 ሒሳብ ዓመትን በስኬት ማጠናቀቁን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ለዚህ ተግባራዊ ስኬት ውድ ባለአክሲዮኖቻችን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ፣ በሥራ አመራር ቦርድ አባላት ላቅ ያለ የቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ አመራር ለሰጣችሁ የስራ አመራር ቦርድ አባላት  እንዲሁም ለውጤት የምትተጉ ቅርንጫፎቻችን፣ የተቋማችን የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከምንም በላይ ግን የሒሳብ ዓመቱ ስኬት ዋነኛ ባለቤቶች የሥራ ፈጠራና የለውጥ የቢዝነስ ሥራ አንቀሳቃሽ፣ አርሶ አደር እና ወጣት ሴቶች ደንበኞቻችን ናቸው። በያዝነው የሒሳብ ዓመት የተቋማችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና መላው ሠራተኞች ጠንካራ ጎኖቻችንን በማጎልበት እና የነበሩንን ውሱንነቶች በማሻሻል፣ መልካም አጋጣሚዎችን በንቃት በመጠቀም፣ እንዲሁም ከፊታችን የሚደቀኑ ፈተናዎችን በማሸነፍ፣ አሰራራችንን በኮርባንኪንግ እና በዲጂታል ባንኪንግ በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለራዕያችን መሳካት በትጋት እንደምንሰራ ቃል እየገባን፣ የተለመደው የደንበኞቻችን እና የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር እንዳይለየን በማክበር እጠይቃለሁ። ለተገኘው ስኬት ዋነኛ ተዋናይ ለሆናችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን፣  የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ለባለአክሲዮኖች እና ለውድ ሠራተኞቻችን ያለኝን ላቅ ያለ ምስጋናዬ እያቀረብኩ፣ አዲሱ የሂሳብ ዓመት ቀጣይነት ያለው ዕድገት የምናሳይበት እንዲሆን እመኛለሁኝ። ስኬትን በተግባር!

እንኳን ደስ አላችሁ!እንኳን ደስ አለን! Read More »

Scroll to Top