Articles

this post is only for latest Articles

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር አርቲስት ይገረም ደጀኔን እና አርቲስት ትዕግስት ግርማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር አርቲስት ይገረም ደጀኔን እና አርቲስት ትዕግስት ግርማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡   አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር ድርጅቱን ይገልፃሉ ካላቸው  ብራንድ አምባሳደሮች ጋር  ስምምነት ተፈራርሟል።   የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር፣ አርቲስት ትዕግስት ግርማን እና አርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር ማድረጉን አስታውቋል። የአምባሳደርነት ስምምነቱ በዛሬው  እለት የተደረገ ሲሆን፣ ስምምነቱ ለአንድ አመት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል።   የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር፣ አርቲስቶቹን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ የመረጠበት ምክንያት አርቲስቶቹ በስነ-ምግባር የታነፁ፣በስራዎቻቸውም  በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ በመሆናቸው ነው ብሏል።   ከኪነጥበብ ስራዎቻቸውም ባሻገር  ሁለቱም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የሚያደርጓቸው መልካምና ለሌሎችም አርአያ መሆን የሚችሉ እንቅስቃሴዎች የብራንድ አምባሳደርነቱን በሚገባ እንዲወጡ እድል ይፈጥርላቸዋል ብሎ እንደሚያምን አክሲዮን ማህበሩ ገልጧል፡፡   ከተመሰረተ አስር ወራትን ያስቆጠረው አክስዮን ማህበሩ፣ የ1 ሺህ 6 መቶ ሰዎች ሕይወት እንዲሻሻል ማድረጉን የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሮቤል ንጉሴ ተናግረዋል።   የ5 ቢሊየን ብር ካፒታል አክስዮን ከብሔራዊ ባንክ እንደፀደቀለት ያነሱት አቶ ሮቤል አክሲዮኖቹ በሶስት አመት ውስጥ ተሽጦ ያልቃል ብለዋል። የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር አገልግሎቱን በጀመረ በ10 ወር ውስጥ ካፒታሉን ወደ 281 ሚሊየን ብር ማድረሱንም አንስተዋል።   በአንድ አመት ውስጥ ቅርንጫፎቹን 50 ለማድረስ እየሰራ የሚገኘው አክስዮን ማህበሩ፣ አሁን ላይ አዲስ አበባን ጨምሮ በባህርዳር፣ደብረብርሃን፣ሃዋሳ ፣አርባምንጭ ፣ድሬዳዋ እና በሃረር ከተማ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ ስራ ማስጀመሩን አስታውቀዋል።   አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የስራ ዕድል ለመፍጠር፣ የቢዝነስ ክህሎት ሥልጠናዎችን ለመስጠትና የቁጠባና ብድር አገልግሎትን ለማሳደግ አልሞ የተነሳ ተቋም መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፣በተለይም የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የማይችሉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን የማህረተሰብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡   “ስኬትን በተግባር” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተነሳው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት መቋቋም ያቃታቸውና ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ባላቸው አቅም አማራጭ የስራ መስኮችን እንዲመለከቱ ለማስቻል እየሰራ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም ማስታወቁ ይታወሳል፡፡   አክሲዮን ማህበሩ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ፣ በዝቅተኛ ወለድ መጠን ብድር ማቅረብ፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት ያልደረሰባቸውን የገጠር ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ፣ “የቆሎ ተማሪ” የተሰኘ የቁጠባና ብድር አገልግሎት መስጠት፣ የፈጠራና ቱሪዝም ስራዎችን በፋይናንስ መደገፍ ላይ በስፋት እስራባቸዋለሁ ሲል መናገሩም አይዘነጋም፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር አርቲስት ይገረም ደጀኔን እና አርቲስት ትዕግስት ግርማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡ Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባለት የምርጫ ውጤትን ስለማሳወቅ

ዳር 29 /2016 ዓ.ም ደብረብርሃን አጼ ዘርዓ ያዕቆብ አዳራሽ በተከናወነው የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. ባለአክሲዮኖች 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከነበሩት አጀንዳዎች መካከል አንዱ ማይክሮ ፋይናንሱን ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ማከናወን እንደ ነበር ይታወቃል፡፡ በዚሁ መሰረት በእለቱ በተከናወነው የምርጫ ስነ ስርአት አስራ ዘጠኝ ሰዎች የተጠቆሙ ሲሆን ከእነዚህም መካከል በትምህርት ዝግጅት ፣ በስራ ልምድ ፣ በብሄራዊ የባንክ መመሪያ ለእጩ ዳይሬክተርነት የተቀመጡ መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሁም በዳይሬክተርነት ለማገልገል ፈቃደኛ ሆነው ራሳቸውን ለጉባኤተኛው ካስተዋወቁና በመጨረሻ እጩነት ከቀረቡት 19 ተወዳሪዎች መካከል ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 9ኝ እጩዎች ባገኙት የባለአክሲዮን ድምጽ መሰረት እጩ ዳይሬክተር ሆነው የተመረጡ ሲሆን 3ቱ ተጠባባቂ እጩ ዳይሬክተሮችም ተመርጠዋል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ምርጫ በኢትዮጽያ ብሔራዊ ባንክ ጸድቀው የስራ ርክብክብ እስከሚደረግ ድረስ ውጤቱን ለባለ አክሲዮኖች በሙሉ ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ በዚህ መሰረት እንዲቀመጥ አድርጓል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ዕጩ ያገኙት ድምፅ   ተመራጭ ያገኙት ድምጽ 1 ሮቤል ንጉሴ  ኃይሉ 109759 2 ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ ገ/ሃና 106875 3 አቶ ተፈራ ወ/አገኝ ገድሌ 87651 4 አቶ እምሻው ተፈራ ተክሌ 83859 5 አቶ ከለላው ጎሽሜ ክፍሌ 83502 6 አቶ ጊዜው ሽመልስ ኃ/ማርያም 83123 7 አቶ በሱፈቃድ ተስፋዬ አለማየሁ 82728 8 አቶ ተመስገን ወርቁ ላቀው 79830 9 ሊ/ካ በሃይሉ በቀለ 76680 10 አንበስ ግርማ ወ/መድህን 67992 11 አቶ በየነ አየለ ታምሩ 66573 12 ዲ/ን ወ/ጻዲቅ ቃኘው 65522 13 አለባቸው ጎሽም አዘረፍ 64750 14 አቶ ስንታየሁ አንባቸው 55423 15 መ/ቀ/ገ/ ሀይሌ አየለ 54670 16 አቶ ደበበ ደጀኔ ተሰማ 53123 17 ቀ/ዶ/ ሀይሉ ተረፈ 53041 18 አቶ ጋሻው ጎረምስ ማገር 43012 19 ዲ/ን ወ/ኢየሱስ አየለ አግዝ 41443 የድምፅ ቆጣሪ ስም                                                    ወ/ሮ አሰለፈች ጎሽሜ ክፍሌ ተወካይ አቶ ኃይሉ ጥላሁን ገሰሰ   

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር 2ኛ መደበኛ እና 2ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባለት የምርጫ ውጤትን ስለማሳወቅ Read More »

Scroll to Top