Articles

this post is only for latest Articles

እንኳን ደስ አላችሁ!እንኳን ደስ አለን!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ እ.አ.አ  የ2024/25 ሒሳብ ዓመትን በስኬት ማጠናቀቁን ስንገልፅላችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ለዚህ ተግባራዊ ስኬት ውድ ባለአክሲዮኖቻችን ሁሉን-አቀፍ ድጋፍ፣ በሥራ አመራር ቦርድ አባላት ላቅ ያለ የቢዝነስ ሊደርሺፕ፣ አመራር ለሰጣችሁ የስራ አመራር ቦርድ አባላት  እንዲሁም ለውጤት የምትተጉ ቅርንጫፎቻችን፣ የተቋማችን የሥራ መሪዎችና ሠራተኞች ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። ከምንም በላይ ግን የሒሳብ ዓመቱ ስኬት ዋነኛ ባለቤቶች የሥራ ፈጠራና የለውጥ የቢዝነስ ሥራ አንቀሳቃሽ፣ አርሶ አደር እና ወጣት ሴቶች ደንበኞቻችን ናቸው። በያዝነው የሒሳብ ዓመት የተቋማችን ከፍተኛ አመራሮች፣ የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች እና መላው ሠራተኞች ጠንካራ ጎኖቻችንን በማጎልበት እና የነበሩንን ውሱንነቶች በማሻሻል፣ መልካም አጋጣሚዎችን በንቃት በመጠቀም፣ እንዲሁም ከፊታችን የሚደቀኑ ፈተናዎችን በማሸነፍ፣ አሰራራችንን በኮርባንኪንግ እና በዲጂታል ባንኪንግ በማዘመን ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት ለራዕያችን መሳካት በትጋት እንደምንሰራ ቃል እየገባን፣ የተለመደው የደንበኞቻችን እና የባለድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር እንዳይለየን በማክበር እጠይቃለሁ። ለተገኘው ስኬት ዋነኛ ተዋናይ ለሆናችሁ ክቡራን ደንበኞቻችን፣  የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ለባለአክሲዮኖች እና ለውድ ሠራተኞቻችን ያለኝን ላቅ ያለ ምስጋናዬ እያቀረብኩ፣ አዲሱ የሂሳብ ዓመት ቀጣይነት ያለው ዕድገት የምናሳይበት እንዲሆን እመኛለሁኝ። ስኬትን በተግባር!

እንኳን ደስ አላችሁ!እንኳን ደስ አለን! Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶኒያ የ400000.00(አራት መቶ) ሺ ብር ድጋፍ አደረገ በሁለት አመት ውስጥ ከአርባ ሶስት በላይ ቅርጫፍ ማድረስ የቻለውና ካፒታሉንም ሆነ የባለአክሲዮን ቁጥሩን በከፍተኛ ፍጠነት እያሳደገ ያለው አኩፋዳ ገና በመጀመሪያ ዓመቱ የትርፍ ክፍፍል ማድረግ የቻለ ብቸኛው ተቋም ነው ቢባል ማጋነን አይሆንም ። ሁሉም ማኅበረሰብ ባለአክሲዮን እንዲሆን ህልም ይዞ የተነሳው አኩፋዳ ከ10000.00 (አሥር ሺ) ብር ጀምሮ ባለአክሲዮን መሆን እንደሚቻል በመንገር ጥሪውን ያስተላልፋል ። አገልግሎቱን በኮር ባንኪንግ በማገናኘት ቀልጣፍ ፈጣንና ተደራሽ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል። በሳል በሆኑ ቦርዶችና ዳይሬክተሮች የሚመራው አኩፋዳ በቅርቡ ዋና መስሪያ ቤቱን ለመገንባት ቦታ በመረከብ የግንባታ እንቅስቃሴ ላይ ይገኛል… አኩፋዳ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ያለ ተቋም ሲሆን ሀገራዊ የሀብት ማሰባሰብ አካል ለመሆን በማሰብ  ለመቄዶኒያ  የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን  መርጃ ማዕከል የ400000.00 (አራት መቶ ሺ) ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ስኬትን በተግባር !!!!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ለመቄዶንያ ድጋፍ አደረገ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ።

የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን እሁድ ሕዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም በደብረ ብርሃን ከተማ ደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ በዕለቱም የማይክሮ ፋይናንሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ ካሳሁን ደገፉ የተቋሙን የ2023/24 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ የሥራ እንቅስቃሴና የፋይናንስ አፈጻጸም ሪፖርት ለባለአክስዮኖች አቅርበዋል፡፡ የቦርዱ ሰብሳቢ በጉባዔው እንደገለጹት በዚህ ፈታኝ ወቅት ተቋሙ በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ ጥሩ የሚባል ትርፍ ማስመዝገብ መቻሉንና የሒሳብ ዓመቱን በስኬት ማጠናቀቁን ገልጸዋል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ባቀረቡት ሪፖርት እንዳመለከቱት አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም በሒሳብ ዓመቱ 48 ሚሊዮን ብር ከግብር በፊት ማትረፉን ለባለአክሲዮኑ አቅርበዋል፡፡ ጉባዔውም ከተገኘው ትርፍ ላይ ተቀናሽ የሚደረጉ ወጭዎች ተቀንሰው ለማኅበራዊ አገልግሎት 4% በመመደብ ቀሪውን ትርፍ ለእያንዳንዱ ባለአክሲዮን በሚደርሰው ትርፍ ድልድል መሠረት አክሲዮኑን እንዲያሳድግ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢው ካሳሁን ደገፉ በሰጡት ማሳሰቢያ ሁሉም ባለአክሲዮን ተቋሙን እንዲያጠናክር፣ እንዲደግፍና ያለውን የአክሲዮን ድርሻ እንዲያሳድግ በመጠየቅ ስኬትን በተግባር እንድንኖረው የተቋሙ ባለድርሻዎች ላደረጉት ድጋፍና አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ 3ኛ መደበኛና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ። Read More »

ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ የስብሰባ ጥሪ በኢትዮጵያ ንግድ ህግ አንቀጽ 366፣367፣370፣372፣392 እና 400 እንዲሁም በአክሲዮን ማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 22 እና 23 መሰረት የአኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የባለአክሲዮኖች 3ኛ መደበኛ እና 3ኛ አስቸኳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤውን ህዳር 22 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ በደ/ብርሃን ከተማ በደ/ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ስለሚያካሂድ የተከበራችሁ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻችሁ በተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና ቦታ በጉባኤው ላይ እንድትገኙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ 1. የማህበሩ መረጃዎች የማህበሩ ስም አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ ደ/ብርሃን እምዬ ምኒሊክ ክ/ከተማ አጼዘርዓያቆብ ህንጻ  4ኛ ፎቅ የማህበሩ ዌብ ሳይት https://www.Akufadamf.com የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር AM/BD/3/0004970/2014 የአክሲዮን ማህበሩ አይነት              በማይክሮፋይናንስ ስራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ 254,624,000.00 የአክሲዮን ማህበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ 131,780,000.00 2. የ3ኛ አመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች ማሳሰቢያ፡-   አኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

ለአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ!

“እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን!የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በ2023/24 ሒሳብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ጥሩ ውጤት ማስመዝገቡን አብስሯል፡፡ በቀረበው ሪፖርት መሠረት ባሳለፍነው የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አትርፏል፡፡ ለዚህ ውጤት መመዝገብ ከፍተኛውን ድርሻ ላበረከታችሁ የተከበራችሁ ውድ ደንበኞቻችን፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ እና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ሠራተኞቻችን ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።በሂሳብ ዓመቱ ብር 232 ሚሊዮን አጠቃላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን በዓመቱ ውስጥ የነበረው የወጪ አፈፃመማችን 183 ሚሊዮን ብር ሲሆን 47 ሚሊዮን ብር ትረፍ አትር÷ል፡፡ ለተገኘው ትርፍ ተቋማችን የተገበራቸው የወጪ ቅነሳ ስትራቴጂዎች ትልቅ አስተዋጽዖ አበርክቷል።ተቋማችን በስምንት ክልሎች 42 ቅርንጫፍ በመክፈት ከ95,000 በላይ ደንበኞች ያሉት ሲሆን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.8 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን ከ1.6 ቢሊዮን ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለ8250 ደንበኞች አቅርቧል፤ የተሰጡ ብድሮች ለግል ፍጆታ ብድር፣ ለቢዝነስ ማስፋፊያ፣ ለግብርና ብድር፣ ለቤት መስሪያና ማደሻ እና ለተሽከርካሪ ግዥ ብድር ለማኅበረሰባችን ተደራሽ አድጓል፡፡ተቋማችን በ21 ሚሊዮን ብር ካፒታል ሥራ የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የተከፈለ ካፒታል ብር 136 ሚሊዮን እንዲሁም ጠቅላላ የተቋሙ ሃብት ብር 1.9 ቢሊዮን ደርሷል፡፡የተቋማችን የሦስት ዓመት መሪ ዕቅድን መሰረት አድርጎ እየተተገበረ የሚገኘው የሪፎርም ስራ ፍሬያማ በመሆኑ የተበላሹ ብድሮች በከፍተኛ ሁኔታ ቀንሶ ተቋማችን ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ ተቋም እንዲሆን፤ እንዲሁም የወጪ ቅነሳ እንቅስቃሴያችን ውጤታማ እንዲሆን አስችሏል። ተቋማችን አገልግሎቶቹን ለደንበኞቻችን ምቹ እንዲሆኑ ለማስቻል የኮር ባንኪንግ እና አዳዲስ የድጅታል ባንኪንግ አገልግሎቶችን በመዘርጋት እውን ለማድረግ ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህም ለደንበኞቻችን አገልግሎትና ተያያዥ ሥራዎች መቀላጠፍ ጉልህ አስተዋፅኦ በማበርከት ወጪን ለመቀነስ ያስችላል።በሌላ በኩል ባጠናቀቅነው ሂሳብ ዓመት የተቋማችን ዘርፈ ብዙ ተግዳሮቶች የገጠሙት ቢሆንም፣ እነዚህን ተግዳሮቶች በመቋቋም ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻላችን የተቋማችንን ጥንካሬ ብሎም አይበገሬነት ማሳያ ነው።በተገኘው አመርቂ ውጤት በመበረታታት በአዲሱ ሒሳብ ዓመት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በበለጠ ተነሳሽነትና ትጋት መስራት ይጠበቅብናል።የተቋማችን የዳይሬክተሮች ቦርድ እና ሥራ አመራር አባላት የሚሰጡትን አቅጣጫ መሰረት በማድረግ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና የላቀ አገልግሎት በማቅረብ የደንበኞቻችንን እርካታ ከፍ ለማድረግ በትጋት እየሠራን ሲሆን በመጨረሻም ደንበኞቻችን አብራችሁን በመሆን ለውጤቱ መሳካት ላበረከታችሁት አስተዋፅኦ በድጋሚ እያመሰገንን፣ በ2017 ሂሳብ ዓመትም ተቋማችን ተጨማሪ ቅርንጫፎችን በሁሉም ክልሎች በመክፈት 1.2 ቢሊዮን ብር በላይ አክሲዮኖችን መሸጥ፣ 200,052 ደንበኞችን በማፍራት 3.3 ቢሊዮን ብር የተቀማጭን ገንዘብ በመሰብሰብ ለ20,002 የብድር ደንበኞች 3.6 ቢሊዮን ብር ብድር ለደንበኞች ያቀርባል። እንዲሁም የአክሲዮን ትርፉን በአንድ ሺህ ብር አምስት መቶ ብር ለማከፋፈል በትኩረት እየሠራ ይገኛል፡፡አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስስኬትን በተግባር!

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ከታክስ በፊት 47 ሚሊዮን ብር አተረፈ! Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቅያሪ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በደብር ብርሃን ጻድቃኔ ህንፃ 6ተኛ ወለል ላይ የነበረውን የዋና መስሪያ ቤት ቢሮ ወደ አፃ ዘርዐ ያዕቆብ ህንፃ 4ተኛ ወለል ላይ ቀይሯል ፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የዋና መሥሪያ ቤት ቢሮ ቅያሪ አደረገ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አደረገ።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ የዋና መሥሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የአርባ ሁለቱም ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸምና 2017 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት ዕቅድ ሐምሌ 27 እና 28 /2016 ዓ.ም ለሁለት (2) ተከታታይ ቀናት በኢትዮ በርኖስ ሆቴል ገመገመ፡፡ተቋሙ በችግር ዉስጥ ሆኖ እጅግ ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡን በማየት በቀጣይ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን በመክፈት የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ አቅጣጫ ተስጥቷል፡፡ለስኬታችን ክቡራን ባለአክሲዮኖቻችን ፡ደንበኞቻችን የግልና የመንግስት ድርጅቶች ፡የዳይሬክትር ቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ባለድሻ አካላት አበርክቷቸው ከፍ ያለ በመሆኑ በእግዚአብሔር አምላካችን ስም ስናመሰግናችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸም ግምገማ አደረገ። Read More »

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር አርቲስት ይገረም ደጀኔን እና አርቲስት ትዕግስት ግርማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር ድርጅቱን ይገልፃሉ ካላቸው  ብራንድ አምባሳደሮች ጋር  ስምምነት ተፈራርሟል። የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር፣ አርቲስት ትዕግስት ግርማን እና አርቲስት ይገረም ደጀኔን የብራንድ አምባሳደር ማድረጉን አስታውቋል።የአምባሳደርነት ስምምነቱ በዛሬው  እለት የተደረገ ሲሆን፣ ስምምነቱ ለአንድ አመት የሚቆይ እንደሆነም ተገልጿል። የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር፣ አርቲስቶቹን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ የመረጠበት ምክንያት አርቲስቶቹ በስነ-ምግባር የታነፁ፣በስራዎቻቸውም  በማህበረሰቡ ዘንድ ተወዳጅ በመሆናቸው ነው ብሏል። ከኪነጥበብ ስራዎቻቸውም ባሻገር  ሁለቱም የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የሚያደርጓቸው መልካምና ለሌሎችም አርአያ መሆን የሚችሉ እንቅስቃሴዎች የብራንድ አምባሳደርነቱን በሚገባ እንዲወጡ እድል ይፈጥርላቸዋል ብሎ እንደሚያምን አክሲዮን ማህበሩ ገልጧል፡፡ ከተመሰረተ አስር ወራትን ያስቆጠረው አክስዮን ማህበሩ፣ የ1 ሺህ 6 መቶ ሰዎች ሕይወት እንዲሻሻል ማድረጉን የአክሲዮን ማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሮቤል ንጉሴ ተናግረዋል። የ5 ቢሊየን ብር ካፒታል አክስዮን ከብሔራዊ ባንክ እንደፀደቀለት ያነሱት አቶ ሮቤል አክሲዮኖቹ በሶስት አመት ውስጥ ተሽጦ ያልቃል ብለዋል።የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክስዮን ማህበር አገልግሎቱን በጀመረ በ10 ወር ውስጥ ካፒታሉን ወደ 281 ሚሊየን ብር ማድረሱንም አንስተዋል። በአንድ አመት ውስጥ ቅርንጫፎቹን 50 ለማድረስ እየሰራ የሚገኘው አክስዮን ማህበሩ፣ አሁን ላይ አዲስ አበባን ጨምሮ በባህርዳር፣ደብረብርሃን፣ሃዋሳ ፣አርባምንጭ ፣ድሬዳዋ እና በሃረር ከተማ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ ስራ ማስጀመሩን አስታውቀዋል። አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ የስራ ዕድል ለመፍጠር፣ የቢዝነስ ክህሎት ሥልጠናዎችን ለመስጠትና የቁጠባና ብድር አገልግሎትን ለማሳደግ አልሞ የተነሳ ተቋም መሆኑን የገለጹት ሃላፊው፣በተለይም የባንክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የማይችሉና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኙትን የማህረተሰብ ክፍሎች በተመጣጣኝ ወለድ የብድር አገልግሎት ለማቅረብ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ “ስኬትን በተግባር” የሚል መሪ ቃል ይዞ የተነሳው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን እየተከሰተ ያለውን የኑሮ ውድነትና የዋጋ ንረት መቋቋም ያቃታቸውና ልዩ ትኩረት የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች ባላቸው አቅም አማራጭ የስራ መስኮችን እንዲመለከቱ ለማስቻል እየሰራ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም ማስታወቁ ይታወሳል፡፡ አክሲዮን ማህበሩ ወጣቶችንና ሴቶችን ተጠቃሚ ማድረግ፣ በዝቅተኛ ወለድ መጠን ብድር ማቅረብ፣ የፋይናንስ ተቋማት አገልግሎት ያልደረሰባቸውን የገጠር ክፍሎች ተደራሽ ማድረግ፣ “የቆሎ ተማሪ” የተሰኘ የቁጠባና ብድር አገልግሎት መስጠት፣ የፈጠራና ቱሪዝም ስራዎችን በፋይናንስ መደገፍ ላይ በስፋት እስራባቸዋለሁ ሲል መናገሩም አይዘነጋም፡፡ ነሃሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ  አክስዮን ማህበር አርቲስት ይገረም ደጀኔን እና አርቲስት ትዕግስት ግርማን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ ሾመ፡፡ Read More »

እንኳን ለ 2016 ዓ.ም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ!

ለአኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ነባር ባለአክሲዮኖች የቀረበ የተጨማሪ የአክሲዮን ግዢ ጥሪ! በመሆኑም በሀገሪቱ የንግድ ሕግ ነባር ባለአክሲዮኖች ባላቸው የቅድሚያ መብት መሰረት አዲስ የወጡ አክሲዮኖችን በማይክሮፋይናንሱ ውስጥ ባላችሁ የአክሲዮን መጠን የተደለደለላችሁ ሲሆን መግዛት የምትፈልጉትን አክሲዮኖች ጠቅላላ ዋጋ 25 % ቅድሚያ በመክፈል እስከ መስከረም 15/2016 ዓ/ም ድረስ በማይክሮ ፋይናንሱ የአክሲዮን ሽያጭ እና አስተዳደር ክፍል በመቅረብ እንዲሁም በሁሉም የተቋሙ ቅርንጫፎች በመሄድ እንድትገዙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪ እያቀረበ ተጨማሪ መረጃዎችን በተቋማችን ድህረ ገፅ https://akufadamf.com ላይ በመግባት የተሟላ መረጃ የምታገኙ መሆኑን እየገለፅን የዚህ ታላቅ ዕድል ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በአክብሮት ተጋብዛችኋል። የዳይሬክተሮች ቦርድለበለጠ መረጃአኩፋዳ ማይክሮፋይናንስ ተቋም አ.ማዋና መስሪያቤትጠባሴ ጻድቃኔ ሕንጻ 6ኛ ፎቅአክሲዮን ሽያጭና አስተዳደር ክፍልስ.ቁ፡- 0988999996/97/98/

እንኳን ለ 2016 ዓ.ም በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ! Read More »

Akufada to implement its Core Banking and Digital Banking Systems

Akufada MFI, one of the newest microfinance institutions in Ethiopia, announced that it is in the final stages of procuring its Core Banking and Digital Banking Systems. The systems will enable the institution to offer a range of products and services to its customers, such as savings, loans, insurance, remittances, mobile banking, and Internet banking. The Board Chairman of Akufada MFI, Ato Robel Nigusse, said that the institution is aiming to launch its Core Banking and Digital Banking Systems before the end of 2023. He added that the systems will help the institution to expand its branch network, reach more customers, improve operational efficiency, and comply with regulatory requirements. Akufada MFI was established in 2022 with 33 million Br paid-up capital with its head office in Debre Birhan. It currently has sixteen branches in North Shewa, Debre Birhan, Hawasa, Bahirdar and Addis Ababa. It plans to increase its branches to 50 in the FY 2023/24 and its capital to 5 Billion Br by 2025.

Akufada to implement its Core Banking and Digital Banking Systems Read More »

Scroll to Top