አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ የዋና መሥሪያ ቤት አመራሮችና ሠራተኞች እንዲሁም የአርባ ሁለቱም ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጆች በተገኙበት የ 2016 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት አፈጻጸምና 2017 ዓ.ም ሒሳብ ዓመት ዕቅድ ሐምሌ 27 እና 28 /2016 ዓ.ም ለሁለት (2) ተከታታይ ቀናት በኢትዮ በርኖስ ሆቴል ገመገመ፡፡
ተቋሙ በችግር ዉስጥ ሆኖ እጅግ ውጤታማ አፈጻጸም መመዝገቡን በማየት በቀጣይ ተጨማሪ አዳዲስ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቶችን በመክፈት የላቀ ውጤት እንዲመዘገብ አቅጣጫ ተስጥቷል፡፡
ለስኬታችን ክቡራን ባለአክሲዮኖቻችን ፡ደንበኞቻችን የግልና የመንግስት ድርጅቶች ፡የዳይሬክትር ቦርድ አመራሮችና ሰራተኞች እንዲሁም ባለድሻ አካላት አበርክቷቸው ከፍ ያለ በመሆኑ በእግዚአብሔር አምላካችን ስም ስናመሰግናችሁ በታላቅ ደስታ ነው፡፡