አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ እና የሰሜን ሸዋ ዞን ትምሕርት መምሪያ በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

በዞኑ ውስጥ የሚገኙ ትምሕርት ቤቶችን፣ መምሕራንን እና ተማሪዎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ዛሬ ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በደብረብርሃን ከተማ ተፈራርመዋል።


ስምምነቱ በዋናነት በአገር ልማት እና ማኅበረሰብ ዕድገት ላይ እየሰሩ በሚገኙት በሁለቱ ተቋማት መካከል የዳበረ ሐብት አስተዳደር እና የፋይናንስ አቅርቦት ላይ በትብብር ለመስራት ያለመ ነው።


በዚህ የመግባቢያ ስምምነት መሠረት በጥቅል ልማትና ማኅበረሰብ ዕድገት፣ በተቋሞቻቸው ሀብት አስተዳደርና ትብብር፣ በተመጋጋቢ ፕሮሞሽን፣ ገጽታና አቅም ግንባታ ዘርፍ በጋራ ለመስራት በማሰብ ነው።


የዞኑ ትምሕርት መምሪያ ም/ኃላፊ አቶ ዋሲሁን ብርሃኑ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ ተቋሞቻቸውን ወክለው ስምምነቱን የፈረሙ ሲሆን፣ ከጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮም ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል።


በዞኑ ከ1,119 በላይ ትምሕርት ቤቶች ያሉ መሆኑን የጠቀሱት ም/መምሪያ ኃላፊው፣ በእነዚህ የትምሕርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ መምሕራን እና ተማሪዎችን ጨምሮ ትምሕርት ቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ስትራቴጂያዊ ስምምነት እንደሆነ ጠቅሰዋል።


የአኩፋዳ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አብርሃም በበኩላቸው የዞኑን የትምሕርት ሥርዓት መደገፍ እና የፋይናንስ አገልግሎት ማቅረብ የተቋሙ ተልዕኮ በመሆኑ አጠናክረን በአገር አቀፍ ደረጃ የሚተገበር መሆኑን አብራርተዋል።


አኩፋዳ በ7 ክልልሎችና ከተማ አስተዳደሮች 45 የነበሩትን ቅርንጫፎች ወደ 55 እያሳደገ ሲሆን ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራ መሆኑን ጨምረው ገልጸዋል።


አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ
ስኬትን በተግባር!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top