አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በዓመታዊው የዕቅድ አፍፃፀም ግምገማ መድረክ ላይ በ2025/26 በጀት ዓመት በአጠቃላይ የሥራ አፈፃፀም የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ቅርንጫፎች እውቅና ሰጠ።
የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ እና የተቋሙ ተ/ዋና ሥራ አስፍፃሚ አቶ ካሳው ሓይሉ ለተሸላሚዎቹ የዋንጫ፣ ሜዳሊያ እና የእውቅና ሠርተፍኬት አበርክተዋል።
ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ በዕውቅና አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ በ2025/26 በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገቡን አስታውሰው፣ በቀጣይም መላው የተቋሙ ማኅበረሰብ በሁሉም መመዘኛዎች ከዚህ የተሻለ ውጤት ለማስመዘገብ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ሐምሌ 10 እና 11 በኢትዮ በርኖስ ሆቴል የተካሄደው ዓመታዊ የሥራ አፈፃፀም ግምገማ እና የስትራቴጂ ዕቅድ ትውውቅ መድረክ የተቋሙ የቦርድ አባላት እና ተ/ዋና ሥራ አስፈፃሚ ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት እና ቀጣይ የሥራ አቅጣጫ መመሪያዎችን በመስጠት ተጠናቋል።
ስኬትን በተግባር!
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

