የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን መቋቋሙ እና በኢትዮጵያ የተመዘገቡ ከሃምሳ (50) በላይ ባለአክሲዮን ባላቸው ማኅበራት (ኩባንያዎች) በባለ ሥልጣኑ መመዝገብ እንዳለባቸው የሚያስገድድ መመሪያ መውጣቱ ይታወቃል፡፡ በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የመመዝገብ ግዴታ ያለበት የአክሲዮን ማኅበር እስከ ኅዳር 16 ቀን 2018 ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ. እስከ November 25/2025 ድረስ የመመዝገብ ግዴታ የተጣለበት ሲሆን ከኅዳር 17 ቀን 2018 ዓ/ም ወይም እ.ኤ.አ. እስከ November 26/2025 ጀምሮ ምንም ዓይነት የአክሲዮን ሽያጭ፡ ዝውውርና የውስጥ ግዥ በፍፁም የተከለከለ መሆኑን እና ይህ ሳይሆን ቢቀር በወንጀል ጭምር የሚያስቀጣ መሆኑን ባለሥልጣኑ አሳውቋል፡፡ በዚሁ መሠረት ኩባንያችን አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አክሲዮን ማኅበር በአሁኑ ሰዓት በምዝገባ ሂደት ላይ የሚገኝ በመሆኑ ምዝገባው ተጠናቆ ከኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የምዝገባ ምስክር ወረቀት እስከምንቀበል ወይም ባለሥልጣኑ የተለየ መመሪያ አውጥቶ ሽያጭ እስካልፈቀደ ድረስ ማናቸውም የአክሲዮን ግዥ እና ዝውውር የቆመ እና በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ስኬትን በተግባር! አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ

