እንኳን ደስ አለን!​አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ 61ኛ እና 63ኛ ቅርንጫፎቹን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ከተማ ለአገልግሎት ክፍት አደረገ!

የቅርንጫፍ አድማሱን በፍጥነት እያሰፋ የሚገኘው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ፣  ተደራሽነቱን ይበልጥ በማስፋት 61ኛውን ቅርንጫፍ በሰሚት ፍየል ቤት አካባቢ “ሰሚት ቅርንጫፍ” በሚል ስያሜ እንዲሁም 63ኛውን ቅርንጫፍደግሞ ገርጂ ማርያም አካባቢ ” ገርጂ ቅርንጫፍ” በሚል ስያሜ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል።

​ከተመሰረተ አራት ዓመታት ያስቆጠረው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ፣ በእነዚህ ጥቂት ዓመታት ውስጥ እጅግ አስደናቂ ስኬቶችን በማስመዝገብ ከ300 ሺሕ በላይ ደንበኞችን በማፍራት ከ4.6 ቢሊዮን ብር በላይ ተቀማጭ ገንዘብ ማሰባሰብ ችሏል።

​ዝቅተኛ እና መካከለኛ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ለማድረግ ትኩረት ሰጥቶ የሚሰራው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ፣ ተደራሽነቱን በማስፋት በሀገራችን በ7 ክልሎች ከ62 በላይ ቅርንጫፎችን በመክፈት ከ25 ሺሕ በላይ ለሆኑ ደንበኞች ከ5.9 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በተመጣጣኝ ወለድ በመስጠት ተልዕኮውን በማሳካት ላይ ይገኛል።

በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ካሉ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት መካከል ቀዳሚ ለመሆን ራዕይ ሰንቆ በትኩረት የሚሰራው አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ፣ ራዕዩን ዕውን ለማድረግ ተደራሽነቱን በፍጥነት በማሳደግ ላይ ይገኛል::

በሚቀጥለው ሳምንት ደግሞ የተቋሙ 62ኛ ቅርንጫፍ በጀሞ አካባቢ አገልግሎት መስጠት የሚጀምር ይሆናል::

ስለሆነም የተሻለ የቁጠባ ወለድ በሚያስገኙ ባለ ብዙ አማራጭ የቁጠባ ሒሳቦቻችን እንዲሁም በ24 ሰዓት ውስጥ የምንሰጠውን ብሪጅ ብድር ጨምሮ ሌሎች ተመጣጣኝ ወለድ በሚታሰብባቸው የብድር አገልግሎቶቻችን ተጠቃሚ እንድትሆኑ በአክብሮት እንጋብዛለን::

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ
ስኬትን በተግባር!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top