ለተከበራችሁ የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የባለአክሲዮኖች 5ኛ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሕግ አንቀጽ 366 (1) ፣ 367 (1) እና 370 እንዲሁም በማይክሮ ፋይናንሱ መመስረቻ ጽሑፍ
አንቀጽ 20 (20.1) ፣ (20.4) እና (20.5) መሠረት የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አክሲዮን ማኅበር የባለአክሲዮኖች
5ኛ ዓመታዊ መደበኛ እና 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ እሁድ ኅዳር 27 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ
በደብረ ብርሃን ከተማ በሚገኘው ኃይሌ ሆቴል ልቼ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ በመሆኑም የተከበራችሁ የአክሲዮን
ማኅበሩ ባለአክሲዮኖች በዕለቱ በጉባኤው ላይ እንድትገኙልን የማኅበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

  1. ማኅበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፡-
    1.1 የማኅበሩ ስም፡- አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ
    1.2 የአክሲዮን ማኅበሩ አይነት፡- በማይክሮ ፋይናንስ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማኅበር
    1.3 የአክሲዮን ማኅበሩ ዋና መሥሪያ ቤት አድራሻ፡- (1) አማራ ክልል፣ ደብረ ብርሃን ከተማ፣ እምዬ ምኒልክ ክፍለ
    ከተማ፣ ንግስት እሌኒ ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር አዲስ፣ አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ሕንጻ 4ኛ ፎቅ፤ (2) ስልክ ቁጥር፡-
    0116376457/0116376668፣ ፖ.ሳ.ቁ፡- 211 ፣ (3) ድረ ገጽ፡- https://akufadamf.com/
    1.4 የአክሲዮን ማኅበሩ የምዝገባ ቁጥር፡- AM/BD/3/0004970/2014
    1.5 የአክሲዮን ማኅበሩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- 485,732,000
    1.6 የአክሲዮን ማኅበሩ የተከፈለ ዋና ገንዘብ (ካፒታል)፡- 368,699,000
  2. የባለአክሲዮኖች 5ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-
    2.1 እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2026 ድረስ የተፈጸሙ የአክሲዮን ዝውውሮችን እንዲሁም አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን
    መቀበልና ማፅደቅ፤
    2.2 እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
    2.3 እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት የተቋሙን የውጭ ኦዲተር ሪፖርትን ማድመጥ እና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
    2.4 እ.ኤ.አ ከ2026/2027 እስከ 2028/2029 ሒሳብ ዓመት ድረስ የሚያገለግል የውጭ ኦዲተር መሾም እና የሥራ
    ዋጋ ክፍያ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
    2.5 እ.ኤ.አ የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ክፍፍል እና አደላደል ላይ በዳይሬክተሮች ቦርድ የቀረበ
    የውሳኔ ሀሳብን ማድመጥና ተወያይቶ ማፅደቅ፤
    2.6 እ.ኤ.አ የ2025/2026 ሒሳብ ዓመት ከተጣራ ትርፍ ላይ ለዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስለሚከፈል ዓመታዊ
    የትርፍ ድርሻ እና እ.ኤ.አ 2026/2027 ሒሳብ ዓመት ስለሚከፈል ዓመታዊ የሥራ ዋጋ ተወያይቶ ማፅደቅ፤
    2.7 የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩዎች የጥቆማና የምርጫ መስፈርቶችን ተወያይቶ ማጽደቅ፤
    2.8 የዳይሬክተሮች ቦርድ እጩዎች ምልመላና ምርጫ አስፈጻሚ ጊዜያዊ ኮሚቴን ማቋቋም፤
    2.9 ማይክሮ ፋይናንሱን ለቀጣይ 3 (ሦስት) ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫን ማከናወን፡፡
  3. የባለአክሲዮኖች 4ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፡-
    3.1 እ.ኢ.አ. እስከ ኅዳር 20 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ተፈርመው ክፍያ ያልተፈጸመባቸውን አክሲዮኖች ስለመሰረዝ፤
    3.2 በማይክሮ ፋይናንሱ 1ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የማይክሮ ፋይናንሱን ካፒታል ወደ 5 (አምስት) ቢሊዮን
    ብር ለማሳደግ የተወሰነውን ውሳኔ ስለማሻሻል በሚቀርበው የውሳኔ ሐሳብ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
    3.3. ተሻሽሎ በቀረበው የማይክሮ ፋይናንሱ መመስረቻ ጽሁፍ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤የሚሉ ናቸው፡፡
    ማሳሰቢያ፡-
  4. በጉባኤው ላይ በአካል መገኘት የማትችሉ ባለአክሲዮኖች ሥልጣን ባለው የመንግስት አካል ተረጋግጦ በተሰጠ
    ውክልና ወይም በንግድ ሕጉ አንቀጽ 377 መሠረት ጉባኤው ከሚካሄድበት ዕለት 3 ቀናት በፊት በየትኛውም
    የማይክሮ ፋይናንሱ ቅርንጫፍ ወይም በዋና መስሪያ ቤት የፋይናንስና ኢንቨስትመንት ዳይሬክቶሬት
    ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣ ብሔራዊ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ዋናውንና ኮፒ
    ይዘው በአካል በመቅረብ፣ ለዚሁ ዓላማ በተቋሙ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ ሞልታችሁ በመፈረም፣ ተወካይ
    በመሾም በጉባኤው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
  5. ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማኅበሩ ጠቅላላ ጉባኤ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ
    ነው፡፡ እንዲሁም በስራ ላይ ያሉ የማይክሮ ፋይናንሱን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት፣ የማይክሮ ፋይናንሱን
    ሠራተኞች፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚና ከፍተኛ ኃላፊዎች ባለአክሲዮኖችን በመወከል በጉባዔው ላይ መሳተፍ
    የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
  6. ባለአክሲዮኖች ባስመዘገቡት ተንቀሳቃሽ (ሞባይል) ስልክ ቁጥር ላይ የባለአክሲዮን መለያ ቁጥር የሚላክ በመሆኑ
    ባለአክሲዮኖች ወይም ተወካዮች ማይክሮ ፋይናንሱ ባዘጋጀው ቅጽ ውክልና ለመስጠትም ሆነ ወደጉባዔው
    ሲመጡ ይህንኑ መለያ ቁጥር ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ድርጅትን ወክሎ የሚቀርብ ተወካይ የድርጅቱ/የማኅበሩ ሥራ አስኪያጅ መሆኑንና ድርጅቱን/ማኅበሩን ወክሎ
    በጉባዔው ላይ ድምጽ ለመስጠት የሚያስችል ሥልጣን ያለው ስለመሆኑ የሚያሳይ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ
    አገልግሎት የተመዘገበ የመመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደንብ ወይም ቃለ ጉባዔ በማስረጃነት ይዞ
    መቅረብ አለበት፣ አልያም በማይክሮ ፋይናንሱ የውክልና ቅጽ መሰረት ውክልና የተሰጠው መሆን አለበት፡፡
  8. አካለመጠን ያልደረሱ (ሕጻናት) ባለአክሲዮኖች ሞግዚት የሆናችሁ ተሳታፊዎች የሞግዚትነት ማስረጃ ወይም
    የሕጻናቱን የልደት የምስክር ወረቀት ዋናውንና ኮፒ ይዛችሁ መቅረብ ይኖርባችኋል፡፡
  9. በሚመለከተው የመንግስት አካል ወይም በማኅበሩ ዋና መስሪያ ቤትም ይሁን በቅርንጫፎቻችን ቀርባችሁ
    ውክልና የምትሰጡም ሆነ በጉባዔው በአካል የምትገኙ ባለአክሲዮኖች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ የቀበሌ
    መታወቂያ ወይም ብሔራዊ መታወቂያ ወይም መንጃ ፍቃድ ወይም ፓስፖርት ይዛችሁ እንድትቀርቡ
    እንዲሁም በውክልና በጉባዔው ላይ የምትገኙ ተወካዮች ማንነታችሁን የሚገልፅ የታደሰ መታወቂያ ዋና እና
    ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ እንድትቀርቡ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡
    ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116376457/0116376668 ይደውሉ፡፡
    የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋም አ.ማ. የዳይሬክተሮች ቦርድ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top