አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ለሐበሻ አረጋውያንና ምስኪኖች መርጃ ልማት ድርጅት የምግብ እሕል ድጋፍ አደረገ

በደብረብርሃን ከተማ የሚገኘው የአረጋውያን መርጃ ድርጅት በርካታ ጧሪ የሌላቸውን አረጋውያን እና ምስኪኖችን ከወደቁበት እያሰባሰበ የሚንከባከብ አገር-በቀል የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው። ሆኖም በሥሩ ከያዛቸው በርካታ ድጋፍ የሚሹ አካላት ቁጥርና የችግሩ ውስብስብነት አንጻር ሰፊ ድጋፍና ዘላቂ የመፍትሔ መንገዶችን ይሻል።

ከእነዚህ ፍላጎቶች አንጻር አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ 10 ኩንታል የምግብ እህል በዛሬው ዕለት ጳጉሜ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በመርጃ ማዕከሉ በመገኘት ድጋፉን ሰጥቷል።ድጋፉንም የአኩፋዳ የዳይሬክተሮች ቦርድ ም/ሰብሳቢ ዲ/ን ካሣሁን ደገፉ ከተቋሙ የማኔጅመንት አባላት ጋር በጋራ በመሆን በሥፍራው ተገኝተው አስረክበዋል።

አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ

ስኬትን በተግባር!

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top