አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ እ.ኤ.አ በ2031 ኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት መካከል መሪ የመሆን ራዕዩን ለማሳካት ከያዛቸው ቁልፍ ተግባራት ውስጥ አንዱ የዲጅታል ሽግግር ነው::
ይህንን ሽግግር ዕውን ለማድረግ የተቋማችንን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ክፍል ቢሮ በአዲስ አበባ ከተማ በማድረግ በሰለጠነ እና ሰፊ ልምድ ባለው የሰው ኃይል የማደራጀት ሥራ በመሠራት ላይ ይገኛል:: በዛሬው ዕለትም ክፍሉን በአዲስ የማዋቀር ሥነ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ተከናውኗል::
ከዚህ በተጨማሪም በአዲስ አበባ እና አካባቢዋ ያሉትን ቅርንጫፎች በተጠናከረ ሁኔታ ለመደገፍ በሚያስችል መልኩ የአዲስ አበባ ማስተባበሪያ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በዛሬው ዕለት በይፋ ሥራ ጀምሯል::
የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ንግግር በማድረግ ያስጀመሩት የተቋሙ የዳይሬክተሮች ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ዲ/ን ካሳሁን ደገፉ፣ የክፍሎቹ በሰለጠነ የሰው ኃይል እና ቴክኖሎጂ መደራጀት የውስጥ አሠራሮችን ለማዘመን፣ የዲጂታል አገልግሎቶችን ለማስፋፋት፣ የመረጃ ደህንነትን ለማጠናከር፣ የውሳኔ አሰጣጥን ለማቀላጠፍ እና ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል::
የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሲራክ ግርማ በበኩላቸው፤ በዛሬው ዕለት ሥራ የጀመሩት ሁለቱም ክፍሎች ለደንበኞቻችን ዘመኑ የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቀላል፣ ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ የተደራጁ ናቸው ብለዋል::
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ
ስኬትን በተግባር!
