በተለምዶ 100 ማኅበራት እየተባሉ ከሚጠሩት አባላት ጋር የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ውይይት አካሄደ
የደብረ ብርሃን ከተማ ከተማና መሠረተ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ነቢዩ ባዩ ተቋማቸው እና መሬት መምሪያ ለ100 የቤት ማኅበራት በቦታ ዝግጅት እና የካሳ ክፍያ አስመልክቶ የተሄደበትን ርቀት ለውይይት መነሻ ሰነድ አቅርበዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ከንቲባ የተከበሩ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው ከተማው ከ2008 ዓ.ም አንስቶ እስከ 2015/16 ዓ.ም ድረስ በብዙ ሺህ ለሚቆጠሩ ዜጎች ቦታ አመቻችቶ የቤት ተጠቃሚ ማድረጉን አስረድተዋል።
በመድረኩም ሰፊ ውይይት ተደርጎ የመሬት ካሳ ግምቱን እስከ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሁሉም የማኅበራት አባላት አስገብተው እንዲያጠናቅቁ አቅጣጫ ተቀምጦ መግባባት ላይ ተደርሷል።
የውይይት ተሳታፊዎችም እስከ መስከረም 15/2018 ዓ.ም ድረስ አስገብተው ለማጠናቀቅ መስማማታቸውን በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል።
በስብሰባው የአኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ ዋናው መሥሪያ ቤት የኦፕሬሽን እና ሪሶርስ ሞቢላይዜሽን ዲቪዥን ሥራ አስኪያጅ አቶ ሥዩም ተፈራ ተገኝተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።
አኩፋዳ ወጣቶች የቤት ባለቤት እንዲሆኑና የተረጋጋ ሕይወት እንዲመሩ ለ100 ማህበራት አባላቶች በተመጣጣኝ ወለድ ብድር ማቅረብ እና ለአባላቱ ቁጠባ ጠቀም ያለ ወለድ እንደሚከፍል ለታዳሚው አብራርተዋል።
አገልግሎቱንም ከመስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በደብረብርሃን ከተማ በሚገኙት 3ቱም ቅርንጫፎች መገልገል እንደሚችሉ ተገልጿል።
ከብድርና ቁጠባ ጋር የተገናኘ የማኅበር አባላት ለሚኖራቸው ጥያቄ ሁሉ:-
+251116377756
+251116377175 ይደውሉ።
ስኬትን በተግባር!

