<<የወረዳችንን ወጣቶችና አርሶ አደሮች በፋይናንስ ተደራሽ ማድረግ በክልል ደረጃ የጀመርነው የ25 ዓመታት ተሻጋሪ የልማት ዕቅድ አስኳል ነው>> ~~ አቶ አከበረኝ አላማው፣ የእንሳሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ እና እንሳሮ ወረዳ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሥምምነት ተፈራረሙ እንሳሮ፣ ለሚ ||
አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ በስትራቴጂ ያስቀመጠውን የፋይናንስ ተደራሽነት እና አካታችነት (Financial Inclusion and Access to Finance for the hard-to-reach communities) ላይ በጋራ ማኅበረሰቡን ለማገልገል ያለመ የትብብር ማዕቀፍ ዛሬ መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ.ም በእንሳሮ ወረዳ ለሚ ከተማ ስምምነቱ ተፈርሟል። ስምምነቱን የእንሳሮ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ክቡር አቶ አከበረኝ አላማው እና የአኩፋዳ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ወዳጆ ተፈራርመዋል። ይህ አጋርነት በዋናነት የወረዳውን ወጣቶችና ሴቶች የኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች፣ የአርሶ አደሮች የግብርና ግብዓት እና የቴክኖሎጂ ግዢ፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና የመኖሪያ ቤት ማኅበራት ብድር ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ትልቅ አስተዋፅዖ እንዳለው የአኩፋዳ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ አብርሃም ገልፀዋል። <<የወረዳችንን ወጣቶችና አርሶ አደሮችን በፋይናንስ ተደራሽ በማድረግ በክልል ደረጃ የጀመርነውን የ25 ዓመታት ተሻጋሪ የልማት ዕቅድ ለማሳካት ዓይነተኛ ሚና አለው፣ አኩፋዳም በተግባር ሕዝባችን ውስጥ ሆኖ እያገለገለን ነው፣>> ያሉት ክቡር አቶ አከበረኝ፣ በጋራ ለጋራ ኤኮኖሚያዊ ዕድገት (shared economy) እንዲረጋገጥ እንሠራለን በለዋል። የኦፕሬሽን ዋና መኮንን አቶ ከፋለ ጣሠው በበኩላቸው ከአገልግሎት ጥራት እና ተደራሽነት አንፃር በቴክኖሎጂ ታግዞ ሕዝቡን ማገልገል ቀዳሚ የአኩፋዳ ፍልስፍና መሆኑን፣ የኦፕሬሽን ልኅቀት (Operational Excellence) ለማምጣት እየተሠራ መሆኑን ለወረዳው መስተዳድር አረጋግጠዋል። አኩፋዳ ማይክሮ ፋይናንስ አ.ማ ስኬትን በተግባር !










